ስለ አክባሪ እህቴ ምክረ ሃሳብ ዝም አልልም!



የቀድሞ የስራ ባልደረባዬ ናት የአማራ ተወላጅ ስትሆን እዚሁ ፊንፊኔ ተወልዳ ያደገች ለወግ ማዕረግ የበቃች የልጆች እናት መሆኗን አውቃለሁ ይህቺ ውድ እህቴ በጣም ጠቃሚ ምክረ ሃሳብ ሰጥታኛለች እጅግ በጣም አመሰግንሻለሁ የማከብርሽና የምወድሽ እህቴ!

በጥቅሉ"በአማርኛ ቋንቋ በምትፅፋቸው መልዕክቶች እኔን እና ሌሎችን እንዳታስቀይም ተጠንቀቅ!ዝም በል አትፃፍ" ብላኛለች

ምክረ ሃሳቧን በማክበር ተቀብያለሁ አማርኛ ሁለተኛ ቋንቋዬ ነው ጥሬ ግሬ የተማርኩት ስለሆነ አፋቸውን በአማርኛ ከፈቱት ወገኖች በማይተናነስበት ሁኔታ አማርኛ መናገርና መፃፍ እችላለሁ የሚል እምነት አለኝ

እና አልፎ አልፎ በምወረውራቸው መልዕክቶች ደስተኛ የማይሆኑ ወገኖች እንዳሉ ባውቅም ይህን ያህል የአማራ ወገኖቼን ጎድቻለሁ የሚል እምነት የለኝም እንዲያውም የተሳሳቱ ወገኖች  ከስህተት መንገድ እንዲመለሱ እገዛ ያደረኩ ይመስለኛል

ለማንኛውም የውድ እህቴን ምክረ ሃሳብ አክብሬ ከልብ በመቀበል ከዛሬ ጀምሮ አፌን በፈታሁበት ቋንቋ በአፋን ኦሮሞ ጠቃሚ ፅሁፎችን አጋራለሁ

ልክ እንደ አንዳንዶች ከኋላ ሆነሽ ጣት ባለመቀሰር ስለመከርሽኝ ለአንቺ ቀድሞም ያለኝ ክብር እጥፍ ድርብ ሆኗል እህቴ እድሜና ጤና ይስጥልኝ

አክባሪና መካሪዋ እህቴ ቅር እንዳይልሽ! https://yaadimedianetwork.blogspot.com/2023/03/blog-post_5.html

Post a Comment

0 Comments