ፊንፊኔ #Ethiopia መጋቢት 09,2015(YMN) ጽንፈኛ ኃይሎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ
አህመድ እየተመራ ያለውን የብልጽግና መንግስት ለመገልበጥ ያግዘናል ያሉትን በርካታ ስልት በመቀየስ ከውስጥና ከውጭ ቅንጅት
በመፍጠር በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ መሆናቸው ተረጋግጧል
ቅንጅቱ ከውስጥም ከውጭም ምን እንደሚመስል በተግባር ታይቷል፤ ይህ ቅንጅት በመደበኛና የማህበራዊ ሚዲያ
ስራዎች የታገዘ መሆኑ ግልፅ ሆኗል
የጽንፈኛው ስትራቴጂዎች በቁጥር 11 መሆናቸው ተለይቷል እነዚህን ስትራቴጂዎች አንድ በአንድ በቅደም
ተከተል በማየት በጉዳዩ ላይ ሙሉ ግንዛቤ መያዝ ጠቃሚ ይሆናል፤በዚህ ጽሁፍ የስትራቴጂዎቹን ምንነት አንድ በአንድ በማንሳት
ተግባራዊ ለማድረግ የተሞከረበትን ሁኔታ በመዘርዘር ጉዳዩን በቅደም ተከተል በማየት የጽንፈኞችን እኩይ ድርጊቶች ማጋለጥ አስፈላጊ
ይሆናል
ስትራቴጂ 1: ሃይማኖትን መሰረት
ያደረገ ግጭት እንዲቀጣጠል ማድረግ
በኢትዮጵያ ውስጥ ቀደም ሲልም በተለያዩ ወቅቶች በተለያዩ ቤተ እምነቶች ውስጥ አንዳንድ እኩይ
ድርጊቶችን በመፈፀም በህብረተሰቡ መካከል የሃይሞኖት ግጭት እንዲፈጠር በማድረግ ሕዝብ እንዲጋጭ ተከታታይነት ያለው ሙከራ
ሲደረግ ቆይቷል
በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎች ቤተ እምነቶች እንዲቃጠሉና እንዲወድሙ በማድረግ የክርስትያንና
እና የእስልምና እምነት ተከታዮች መካከል መጠራጠርና አለመግባባት
እንዲፈጠር ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ መቆየቱ ተጨባጭ ማሳያ ነው
የሁለቱ ሃይማኖቶች ተከታዮች ግን ፅንፈኞቹ በሚፈልጉት ደረጃ አለመግባባት ውስጥ ገብተው ለዘመናት
የተገነባ አብሮነታቸውን ለመናድ ፈቃደኛ ባለመሆን ሁሉንም ጽንፈኞች አሳፍረዋል
ከውጭም ሆነ ከውስጥ ድጋፍ ያለው ኃይል ግን ተስፋ ሳይቆርጥ በቅርቡም በቅድመ ዝግጅት ክንዱን በማጠናከር
በሃይማኖት አባቶች መካከል ተፈጥሮ የነበረውን አለመግባባት እንደ ምቹ አጋጣሚ ለመጠቀም ብርቱ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ
በተግባር እየተመለከትን ነው
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል በውስጣዊ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችና
በቋንቋ አጠቃቀም ላይ የተፈጠረው አለመግባባት በምክክር ዘላቂ መፍትሄ ያገኘ መሆኑ እየታወቀ ለስትራቴጂው ተግባራዊነትና ስኬት
የሚያግዘው በመሆኑ ምንም መፍትሄ ያልተሰጠው አድርጎ በመውሰድ እስከ አሁንም በሚዲያዎች ጉዳዩን የማቀጣጠል ሙከራ እንደማሳያ
የሚወሰድ ነው
በኢትዮጵያ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት የአገር
መሪ፤ታዋቂ የአገር ሽማግሌዎችና ባለጉዳዮቹ የሃይማኖት አባቶች በተሳተፉበት መድረክ ላይ ሰፊ ውይይትና ምክክር ተደርጎበት
መፍትሄ አግኝቷል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
የውስጥ የመልካም አስተዳደር ጉዳይና በተለያዩ ቋንቋዎች የእምነቱ አስተምህሮ ለተከታዮች እንዲደርስ መግባባት ላይ የተደረሰበት
መሆኑ በአደባባይ ይፋ ተደርጓል
የኢትዮጵያ ዜጎች ብሄር ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በያሉበት በሚኖሩበት አካባቢ ሁሉ ያለውን ተጨባጭ
እውነታ በአግባቡ በመረዳት የትኛውም ጽንፈኛ ተልዕኮውን ለመፈፀምና የቅጥረኝነት ጥቅሙን ለማስጠበቅ ሲል በማድረግ ላይ ያለውን
እንቅስቃሴ መከላከል ሰላሙን መጠበቅና መንከባከብ ልማቱን በማስቀጠል የኢኮኖሚ እድገቱን ለማረጋገጥ ቀጣይነት ያለው ጥረት
ማድረግ ይጠበቅበታል
መንግስትና ሁሉም መንግስታዊ አካላት የፀጥታ ተቋማት ሚናቸውን መወጣት የሚችሉት ህብረተሰቡ ያለውን
አጠቃላይ ሁኔታ በመረዳት የበኩሉን እገዛ ማድረግ ሲችል ብቻ ነው፤ለማስታወስ ካልሆነ በስተቀር ይህ እውነት ለኢትዮጵያ ሕዝብ
የሚነገር አይሆንም
በኢትዮጵያችን ውስጥ በጥቅመኞች ቅንጅትና መናበብ ምክንያት ብዙ ሰው ሰራሽ አደጋዎች ተፈጥረው አልፈዋል፤የለውጡ
መንግስት ያልተገደበ ትዕግስት በማሳየቱ ህዝብም አልበገርም ብሎ በአንድነት በመቆሙ የፀጥታ ኃይሎች ከፍተኛ መስዋትነት
በመክፈላቸው ኢትዮጵያ መፍረስ የማትችል ጠንካራ አገር መሆኗን በተግባር አረጋግጣለች
ይህን ድል ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች ተመልክተዋል ኢትዮጵያዊያን በሚሰጠው አጀንዳ እንዲከፋፈሉ፤እንዲሁም
በመጨረሻ ላይ ሰላም አጥተው ከአገራቸው እንዲሰደዱ፤በአጠቃላይ ኢትዮጵያ እንድትፈርስ የመደቡት በጀት ሁሉ ምንም ዋጋ
ሳያስገኝላቸው ቀልጦ ቀርቶባቸዋልⵆበዚህም
ምክንያት ቁጭት ውስጥ በመግባት ተጨማሪ ጉዳት እንዲደርስ ቀጣይነት ያለው ጥረት ማድረጋቸው ስለማይቀር ለኢትዮጵያችን ሉዓላዊነት
መከበር ሁላችንም የዜግነት ግዴታችንን መወጣት ይጠበቅብናል!ቀጣዩን የጽንፈኞች ስትራቴጂ ይዤ እመለሳለሁ መልካም ቆይታ ሰላም ይብዛልን!
0 Comments