ፊንፊኔ #Ethiopia መጋቢት 15,2015(YMN) የአዲስ አበባ ፖሊስ በአንድ አካባቢ የሚኖሩ 7 ታዳጊዎች እንደጠፉ እና እንደታገቱ ተደርጎ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እና ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለው መረጃ እውነትነት የጎደለውና የተዛባ ነው አለ።
ፖሊስ መረጃው እውነትነት የጎደለውና የተዛባ ስለመሆኑ አረጋግጥላችኃለሁ ብሏል።
ታዳጊዎቹ በአሁኑ ወቅት በፖሊስ ስር እንደሚገኙም ገልጿል፡፡
ፖሊስ ምን አለ ?
- አራት ወንድ እና ሦስት ታዳጊ ሴቶች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 " መካኒሳ ቆሬ " አካባቢ ከሚገኘው የወላጆቻቸው መኖሪያ ቤት እንደጠፉ እና ታግተዋል በሚል በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እና ማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው መረጃ ትክክል አይደለም።
- ታዳጊዎቹ ለመጥፋት በማሰብ ከወላጆቻቸው መኖሪያ ቤት ልብሶቻቸውን ይዘው እንደወጡ እና በልዩ ልዩ ምክንያቶች ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለው መኖር እንደሚፈልጉ በሰጡት ቃል ገልፀዋል።
- በልመና ተግባር ላይ ተሰማርተውም ባገኙት ገንዘብ የተወሰኑ የቤት ቁሳቁስ በማሟላት ሰባቱም በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው " ቡልቡላ " አካባቢ በ1 ሺ 800 ብር መኖሪያ ቤት ተከራይተው #ሦስቱ ወንዶችና ሦስቱ ሴቶች የፍቅር ግንኙነት በመመስረት በጋራ እየኖሩ እንደሚገኙ እራሳቸው በሰጡት ቃል ተናግረዋል።
- የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባትና ከተለያዩ ቦታዎች መረጃ በማሰባሰብ በተደረገው ክትትል ያሉበትን ቦታ እና ሁኔታ ማወቅ ተችሏል።
- ታዳጊዎቹ የስነ-አእምሮና ተያያዥ የጤና ምርመራ እንዲያገኙ እንዲሁም ማህበራዊ ችግራቸው ሊፈታ በሚችልበት ሁኔታ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ ነው።
- አንዳንድ መገናኛ ብዙኃንና ማህበራዊ ሚዲያዎች መረጃን ስላገኙ ብቻ የሚያስከትለውን አሉታዊ ጫና ታሳቢ ሳያደርጉ ዜናውን ማሰራጨታቸው በህብረተሰቡ የእለት ከእለት እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ጫና የሚያስከትል መሆኑን ግምት ውስጥ ማስገባት እንደሚጠበቅባቸው ሊገነዘቡ ይገባል።
- ወንጀልን በማጣራት እውነትን የማፈላለግ የምርመራ ስራ ጊዜን የሚጠይቅ ተግባር መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።
(አዲስ አበባ ፖሊስ)
Source (tikvahethiopia)
0 Comments