ፊንፊኔ #Ethiopiaየካቲት 26, 2015 (YMN) በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚደረገውን ድጋፍ አስመልክቶ ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ ማሳሰቢያ
የክልሉ መንግስት ማሳሰቢያ እንደሚከተለው ቀርቧል
በክልላችን የተለያዩ ዞኖች ውስጥ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በሰውና እንስሳት ላይ ያጋጠመው የምግብና ውሃ እጥረት ችግር መፍትሄ እንዲያገኝ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ለህብረተሰቡና ለተለያዩ አካላት የድጋፍ ጥሪ ያቀረበ መሆኑ ይታወሳል
በቀረበው ጥሪ መሰረት ግለሰቦች፤የመንግስት ተቋማት፤መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ሰፊው ህብረተሰብ አስደናቂ በሆነ ሁኔታ ለቀረበው ጥሪ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ላይ ይገኛል፤ለዚህም መንግስት ምስጋናውን ያቀርባል
በዚሁ መሰረት እየተሰበሰበ ያለው ሃብትና ገንዘብ በተቀናጀ፤ፈጣንና ፍትሃዊ በሆነ ሁኔታ ድጋፍ ለሚፈልግ ህብረተሰብ እንዲቀርብ በማዕከል ይህን የድጋፍ ስራ እንዲመራና እንዲያስተባብር ስልጣን በተሰጠው የኦሮሚያ ቡሳ ጎኖፋ መመራት እንዳለበት ይታወቃል
ስለዚህ ግለሰቦች፤ቡድኖች፤መንግስታዊ ተቋማት፤የንግድ ድርጅቶች፤ ማህበራትና የመሳሰሉት በድርቅ ምክንያት ለረሃብ በተጋለጠው የህዝባችን ስም የሰበሰባችሁትንና ለመሰብሰብ ያቀዳችሁትን ሃብትና ገንዘብ ጨምሮ የተሰበሰበውን ገንዘብ የኦሮሚያ ቡሳ ጎኖፋ ቀደም ሲል ይፋ ባደረጋቸው የባንክ አካውንቶች ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጋችሁበትን ደረሰኝ/bank slip/ ይዛችሁ ከየካቲት 27-28, 2015 ዓ.ም ፊንፊኔ ሳሪስ አዲስ ጎማ ፊት ለፊት በሚገኘው የኦሮሚያ ቡሳ ጎኖፋ ዋና ጽህፈት ቤት እንድትመዘገቡ እናሳውቃል
በቀጣይ ረቡዕ የካቲት 29 2015 ከሰዓት በኋላ ከ10 ሰዓት ጀምሮ በኦሮሚያ ርዕሰ መሰተዳድር ጽህፈት ቤት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና እንግዶች በተገኙበት የርክክብ፤የዕውቅና መስጠትና ለህዝብ ይፋ የማደረግ ስነ ስርዓት የመጀመሪያ ዙር ስለሚካሄድ ማስረጃችሁን ይዛችሁ እንድትገኙ እናሳስባለን
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911 48 86 10 መደወል ይችላሉ
ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
የቦረናን ሕዝብ ለመደገፍ ቀጥሎ የቀረቡ የባንክ አካውንቶችን ይጠቀሙ፤ቁጥሮችን ይፋ ያደረገው የኦሮሚያ ቡሳ ጎኖፋ ነው
1. ሲንቄ ባንክ 1029565101201
2. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000007343756
ለወገን ደራሽ ወገን ነው!

0 Comments