በፊንፊኔ 56 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመስርቷል




ፊንፊኔ #Ethiopia ሚያዝያ 06,2015(YMN) በፊንፊኔ አዲስ አበባ ከ43 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ ሕገ ወጥ መሬት መታገዱ ተነግሯል

የፊንፊኔ አዲስ አበባ ፀረ ሙስና ኮሚቴ ያከናወናቸውን ስራዎች አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል
ኮሚቴው ከሕዳር 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘ 43 ሺህ 436 ነጥብ 44 ካሬ ሜትር መሬት ማገዱን አስታወቋል
የኮሚቴው ሰብሳቢ እና የፊንፊኔ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊድያ ግርማ እንዳሉት እገዳው በምርመራ ወቅት የተሰበሰቡትን ማስረጃዎች መሰረት በማድረግ የተከናወነ ነው
56 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መመስረቱም ተነግሯል መልካም ጅምር ነው! ፊንፊኔ አዲስ አበባ ባህር ናት በባህሩ ውስጥ ደግሞ የተለያዩ ወንጀሎች ይፈፀማሉ እየተፈፀሙም ነው ጅምሩን በማጠናከር ፊንፊኔ አዲስ አበባችን ከየትኛውም ወንጀል የፀዳች እንድትሆንልን በቁርጠኝነት መስራት ተገቢ ነው ያዝ ለቀቅ ሞቅ ቀዝቀዝ ይቁም!
በሌሎች ክልሎች የተቋቋሙ የፀረ ሙስና ኮሚቴዎችስ እስከ አሁን ምን ሰሩ? ያከናወኗቸውን ተጨባጭ ስራዎች ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል አሊያ የፀረ ሌብነቱ ትግል ተዳፍኖ ሊቀር ይችላል
በተጨባጭ ስራ ከተከናወነ ለሕዝብ የሚነገር ነገር አይጠፋም ዝምታው ባለመስራት ምክንያት ሊሆን ስለሚችል መንግስት ቀደም ሲል ባስቀመጠው ግልፅ አቅጣጫዎች መሰረት እንደተሰራ ሁሉም ማረጋገጥ ይጠበቅበታል
የኮሚቴነት ስም ይዞ መቀመጥ ለሕዝብ የሚጠቅም ሊሆን አይችልም
የፀረ ሌብነቱ ትግል ከየት ተነስቶ የት እንደደረሰ መታወቅ አለበት፤ይህ ሲሆን ሰፊው ሕዝብ በአስተማማኝ ሁኔታ በመሳተፍ ለመንግስት ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ ይችላልና ይታሰብበት
የመገናኛ ብዙሃንም ከያዝ ለቅቅ አካሄድ በመውጣት በፀረ ሙስና ትግሉ ምን ደረጃ ላይ እንደተደረሰ ጥብቅ ክትትል በማድረግ አስፈላጊ መረጃዎችን ለአድማጭ ተመልካች ማድረስ ግዴታቸው መሆኑን ተረድተው መስራት ይጠበቅባቸዋል ፈራ ተባ ማለት አይገባም!
ሌቦች  በኔትወርክ ተደራጅተው የሚፈፅሙት ወንጀል የመገናኛ ብዙሃን ተቋማትና በውስጣቸው በሚገኙ ባለሙያዎች ላይም ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሱ መሆናቸውን በመገንዘብ በትጋት መስራት ያስፈልጋል

Post a Comment

0 Comments