የኢትዮጵያን ግጭት በመዘገብ የሚፈነድቁ የቢቢሲ ጋዜጠኞች

 



ፊንፊኔ #Ethiopia ሚያዝያ 03,2015(YMN) ቢቢሲ የሚባለው ዓለም አቀፍ የእንግሊዝ ሚዲያ የኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካ አገራትን መልካም ጉዳይ አይዘግብም፤ዋና ትኩረቱ ግጭት ላይ ነው ቢቢሲ ስለ ልማትና የኢኮኖሚ ዕድገት ስለ መልካም የአገር ክንውኖች ተሳስቶ እንኳ የሚዘግብበት ሁኔታ ፈፅሞ የለም

በዚህ የሚዲያ ተቋም ውስጥ የሚሰሩ ጋዜጠኞች ወደ ሚዲያው ተቋም ሲቀላቀሉ ከግጭት ጉዳዮች ውጭ አልዘግብም በማለት ቃለ መሃላ ፈፅመው የሚገቡ ይመስለኛል ተግባራቸው በዚህ ድምዳሜ ላይ እንድደርስ አስገድዶኛል፤ ከጥቂት  ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ሶስት ቋንቋዎች በአማርኛ በአፋን ኦሮሞና በትግርኛ መዘገብ ሲጀምሩ የነበረኝ መልካም ግምት አሁን ብን ብሎ ጠፍቷል 

የዚህ ተቋም ጋዜጠኞች ግጭት ሲፈጠር ሰርግና ምላሸ ይሆንላቸዋል ለአሁኑ የቢቢሲ ጋዜጠኞች ትኩረቴ ሆኑ እንጂ በአጠቃላይ የምዕራቡ ዓለም የሚዲያ ተቋማት ጋዜጠኞች ስለ ኢትዮጵያና ሌሎች የአህጉራችን መልካም ጉዳዮች ተከታትለው እንደማይዘግቡ በበርካታ ኩነቶች ምክንያት ካረጋገጥን ቆይተናል

ለማንኛም እነዚህ ቅጥረኛ ጋዜጠኞች በጎንደር በደሴና ደብረ ብርሃን የተጣሉ ክልከላዎችን እንዴት እንደዘገቡና ፍላጎታቸውንም እንዴት እንዳካተቱበት የዛሬ ጠዋት ዘገባቸውን በማንበብ ይገንዘቡ https://www.bbc.com/amharic/articles/c6pq16dm30zo




Post a Comment

0 Comments