ፊንፊኔ #Ethiopia ሚያዝያ 06.2015(YMN) የአሌክስ ዲዋል ማንነትና ፍላጎት በጦርነቱ ወቅት
ታውቋል ገብረ ክርስቶስ ገብረስላሴም ከማን ወገን እንደሆነ እናውቃለን ሩንዳሳ እሼቴ የተባለውም በቤት ግንባታ ስራ ላይ
በሸሪክነት የሚሳተፍ ሰው መሆኑን ግለሰቡ ላይ ያተኮረው ማስረጃ ያመለክታል
እነዚህ ግለሰቦች የጠቅላይ ሚኒስትሩ የዶክትሬት መመረቂያ ፅሑፍ የተጭበረበረ ነው ከሌላ የተቀዳ ነው
በሚል የዶክትሬት ድግሪያቸውን ለማሰረዝ ወይም ለማሳገድ በቂ ማስረጃ አግኝተናል በማለት ከሰሞኑ ባወጡት ጽሑፍ ከሰዋል
በግለሰቦቹ የተዘጋጀው ስም የማጥፋት ውንጀላ የዓለም
ሰላም ፋውንዴሽን ተብሎ በሚታወቅ ተቋም ድረ ገፅ ላይ ከሰሞኑ ወጥቷል፤እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ሚያዝያ
05 2023 ከሁለት ሳምንት በፊት በድረ ገፁ ላይ የወጣው ጽሑፍ ከላይ በጠቀስኳቸው ሰዎች አማካኝነት የተዘጋጀ መሆኑ ተጠቅሷል
የሚገርመው የእኛዎቹ ሚዲያዎች ይህን
ክስ ምንም ነገር ሳይመረምሩና ሚዛናዊም ሳያደርጉ እንዳለ ገልብጠው ማቅረባቸው ነው ለምሳሌ “አዲስ ማለዳ” የተባለ ድረ ገፅና ጋዜጣ “የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን የዶክተሬት ዲግሪ ለመሰረዝ በቂ ማስረጃ መኖሩ ተገለጸ” በማለት ቀጥሎ ያለውን ዘግቧል
“ሐሙስ ሚያዚያ 5 ቀን 2015 (አዲስ
ማለዳ) ጥያቄ
ሲነሳበት የነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የዶክተሬት ዲግሪን ሊያሰርዝ የሚችል በቂ የጥናት “ስርቆት” ማስረጃ
ማግኘቱን የዓለም ሰላም ፋውንዴሽን አስታወቀ፡፡
የመመረቂያ ጥናቱ “Social
Capital and its Role in Traditional Conflict Resolution: The Case of
Inter-religious Conflict in Jimma Zone of the Oromia Regional State in
Ethiopia” በሚል ርዕስ የተሰራ ሲሆን፤ የጥናቱ ትኩርት ማኅበራዊ ካፒታል በባህላዊ የግጭት አፈታት ውስጥ ያለው ሚና ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡
“ፕላጂያሪዝም”
የሰውን ጽሑፍ ወይም ሥራ መስረቅ ወይም የራስ አስመስሎ ማቀረብ የሚል ተቀራራቢ ትርጉም የሚሰጠው ሲሆን፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥናትም ይህ አይነቱ ችግር እንደታየበት ፋይንደሽኑ ይፋ ባደረገው ጽሑፍ አስታውቋል፡፡”ሲል በዚህ መልኩ ዘግቦት ለአንባቢዎቹ አቅርቧል(የአዲስ ማለዳ ጽሑፍ ከዚህ የሰፋ ነው)
ይህ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች አሳሳቢ አካሄድ
ነው፤የውጭ ሃይሎች የራሳቸው ፍላጎት አላቸው ፍላጎታቸውን ለማሳካት የማያደርጉት ጥረት የለም ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን በመጠቀም የሚፈልጉትን
ከግብ ማድረስ ጠንክረው ይሰራሉ፤ቢቢሲ፤ሲኤንኤን፤ሮይተርስና ሌሎችም በብሮድካስትና በህተመት ይዘቶቻቸውን የሚያሰራጩ ሚዲያዎች የጌቶቻቸው
ሃሳብና አመለካከት ተቀባይነት እንዲያገኝ የሚሰሩ ናቸው፤የእኛዎቹ ሚዲያዎች ደግሞ ይህን ሳይገነዘቡ ወይም ሆን ብለው እንዳለ በመተርጎም
ያሰራጫሉ፤እነዚህ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የውጭ ጠላቶች ከወያኔ ጋር በመተባበር በጦርነቱ ወቅት እንዴት ሲዘግቡ እንደቆዩ ማስታወስ
ተገቢ ነው
ከላይ በስም የጠቀስኩትን “አዲስ ማለዳ”ን
ለማሳያ አነሳሁ እንጂ በዚህ መልክ የሚሰሩ በርካታ የአገራችን መገናኛ ብዙሃኖች አሉ ስህተት ነው!
በትኛውም የአገር ውስጥ ሚዲያ ውስጥ
የሚሰራ ጋዜጠኛ በግል አመለካከቱ ምክንያት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና እሳቸው በሚመሩት መንግስት ላይ ቅሬታ ሊኖረው
ይችላል፤ቅሬታና ጥላቻውን ግን በአገኘው አጋጣሚ በሚሰራበት ሚዲያ ተጠቅሞ ማሰራጨት አይጠበቅበትም ነውር ነው!
ከቻለ ለአገሩና መሪው በመወገን መስራት
አለበት ወይም ያገኘውን መረጃ ሚዛናዊ በማድረግ ማቅረብ ይችላል ይህ መብቱ ነው፤ካልቻለ ዝም ማለት አለበት! ከዚህ ባሻገር ያገኘውን
አጋጣሚ በመጠቀም ስም አጥፊ የውስጥና የውጭ ከሳሽ ሃይሎችን መተባበር አይጠበቅበትም ይህ አካሄድ ሊያስጠይቅ ይገባል በተለይም የሚዲያ
ተቋማቱ ኃላፊዎች ተጠያቂነት መኖር አለበት
ከአሁኑ ክስ ጋር በተያያዘ ክቡር ጠቅላይ
ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የዶክትሬት መመረቂያ ፅሑፋቻውን እንደማንኛውም ተመራቂ ማጣቀሻዎችን በመጠቀም ማቅረብ ይችላሉ የጥናት
ጽሑፍ አቀራረብ ሕግና ስርዓትን በመከተል ለጽሑፋቸው ማዳበሪያ ምንጫቸውን
ጠቅሰው ቢወስዱ ችግር ያለው አይመስለኝም
ቀደም ሲል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጠውን የሰላም ኖቬል ሽልማት ለማስነጠቅ የተለያዩ አካላት ጥረት አድርገው
አልተሳካላቸውም ሸላሚው ዓለም አቀፍ ተቋም የሰጠውን ሽልማት እንደማይነጥቅ ቁርጥ ምላሹን ከሰጠ በኋላ ከሳሽ ኃይሎች ዝም ለማለት ተገደዋል
ጦርነቱም በሰላማዊ ስምምነት በመጠናቀቁ ምክንያት የመክሰሻ ምክንያቶች ሲሟጠጡ አሁን ደግሞ የመመረቂያ ጽሑፍን
ለማሰረዝ መጡ
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሚመሩት የኢትዮጵያ መንግስት ጠንካራ ሆኖ እስከ ቀጠለ ድረስ የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር በተለያዩ የአገር ውስጥና የውጭ ኃይሎች የሚቀርበው ክስ አይቀርም ይቀጥላል
እነ ማርቲን ፕላውት፤አሌክስ ዲዋልና ሌሎችም በጦርነቱ ወቅት ለወያኔ ወግነው ምን ሲሰሩ እንደቆዩ የሚያውቅ
ጋዜጠኛ ግን የእነሱን ፍላጎት ከግብ ለማድረስ በመተባበር የሃሰት ፕሮፓጋንዳቸውን እንዳለ ገልብጦ አያቀርብም ጥንቃቄና ተጠያቂነት
ሊኖር ይገባል! ምክንያቱም እነርሱ ሊያፈርሷት በሚፈልጓት ኢትዮጵያ ውስጥ እየኖርን ከእነርሱ ጋር መተባበር ራስን መኖሪያ ማሳጣት
እንደሆነ በበቂ ደረጃ በመገንዘብ መስራት ያስፈልጋል!
0 Comments