በሰርጎ ገቦች ላይ ተገቢ ክትትል ማድረግ ይገባል!

 



ፊንፊኔ #Ethiopia ሚያዝያ 09,2015(YMN) ይህ ዜጋ የልዩ ኃይሎችን አደረጃጀት ከሚቃወሙ ምሁር ተብዬዎች ውስጥ አንዱ ነው

ልዩ ኃይል በሕገ መንግስቱ እውቅና የለውም በሚል የሚቀርበው መከራከሪያ ተገቢ አይደለም የሚል አቋም እንዳለው በአንደበቱ ሲናገር ሰምቼዋለሁ
ዶክተር ሲሳይ መንግስቴ በፊንፊኔ አዲስ አበባ ምክር ቤት ውስጥ ምን ይሰራል? ለዚያውም እኮ የምክር ቤት ወንበር ይዞ የተቀመጠው በብልጽግና ፓርቲ ስም ነው አይ ምሁር!ሁለት ቦታ መቆም ነውር ሊሆን ይገባል! ብልጽግና ውስጥ ሰርጎ ገቦች አሉ ተብሎ ሲነገር እንደዚህ ዓይነት ሰዎች በዓይነ ዕሊናዬ ይመጡብኛል፤ባይበላስ ቢቀር!

ኢህአዴግ ስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት "ምሁር ወላዋይ ነው፤አቋም የለውም" በሚል ምክንያት ምሁራንን ወደ ራሱ አያቀርብም ነበር
ኢህአዴግ በዚህ አቋሙ በአንድ ወቅት የሚተች መሆኑን የሚያውቀው ብልፅግና ምሁራንን ወደ ራሱ በማቅረብ ወደ አባልነትነት እንዲቀላቀሉና የህዝብ ተመራጭም ሆነው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ በክብር መቀመጥ እንዲችሉ አድርጓል መልካም ነው
ብልፅግና ይህን ያደረገው ምሁራን ቀድመው ያወቁና ነገሮችን የተረዱ ናቸው በዚህም ህዝብን ማገልገል ይችላሉ በሚል እምነትና ትክክለኛ ውሳኔ ነው፤ነገር ግን ፓርቲው በቅንነት ያስተላለፈው ውሳኔ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ችግሮችን እያመጣበት እንደሆነ መታዘብ ይቻላል
ከላይ በስም የተጠቀስኩት ዓይነት ሰዎች በብልፅግና ውስጥ በሰርጎ ገብነት ገብተው በመስራት ላይ የሚገኙ መሆናቸውን መጠርጠርና አስፈላጊውን የማፅዳት እርምጃ በወቅቱ መውሰድ ይገባል

Post a Comment

0 Comments