ጄኔራል ሰዓረ መኮንን መታሰቢያ ፓርክና ሐውልት ተመረቀ

 



ፊንፊኔ #Ethiopia ሚያዝያ 14,2015(YMN) የቀድሞ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን መታሰቢያ ፓርክና ሐውልት ዛሬ በአዲስ አበባ ተመርቋል። 

በምርቃቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ፣ ጀኔራል መኮንኖች፣ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች፣ የጄኔራል ሰዓረ መኮንን ቤተሰቦችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል። 

እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ ሐውልቱ በአዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ በስማቸው በተሰየመ ፓርክ ውስጥ ክብራቸውን በሚመጥን መልኩ ተገንብቶ ለምርቃት መብቃቱ ተገልጿል። 

የቀድሞ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን አገር ወዳድ የኢትዮጵያ ልጅ እንደነበሩ ተወስቷል።

ጄኔራል ሰዓረ ከግንቦት 2010 . ሕይወታቸው እስካለፈበት ሰኔ 15/2011 . ድረስ የኢፌዴሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም በመሆን ኢትዮጵያን በታላቅ ታማኝነትና ቅንነት አገልግለዋል።




Post a Comment

0 Comments