ለአቤልና መሰሎቹ ያለኝ ምላሽ!




ፊንፊኔ #ሚያዝያ 15,2015(YMN) እነርሱ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሌላውን ወገን በአስፀያፊ ስድቦች አበሻቅጠው ሲያዋርዱ ውለው የሚያድሩት ተከፍሏቸው ነው ማለት ነው!

አንድ ወዳጄ በውስጥ መስመር "እኔ የምልህ ተከፍሎህ ነው?"የሚል ጥያቄ ሰደደልኝ፤ ምን ማለት ነው አንተ ተከፍሎህ ነው? ስል እኔም ጠየኩት መልስ የለም እምጥ ይግባ ስምጥ አላወኩም በዚያው እብስ አለ ለጥያቄው ምላሽ ሳያገኝ ዝም ብሎ በመጥፋቱ ምላሼን ከብዙሃን ጋር ይወቅ ብዬ በማሰብ እንዲህ ከተብኩለት
እኔ እንደ ግለሰብ ባለኝ ትርፍ ጊዜ የለውጡን አመራር ጥረቶች የሚደግፉ አገሬ ኢትዮጵያን የተመለከቱ አንዳንድ ጽሑፎችን፤በአፋን ኦሮሞና በአማርኛ አርቲክሎችንና ፎቶግራፎችን በራሴ ተነሳሽነት ብቻ የማጋራ አንድ ዜጋ ነኝ፤ ለዚህ ጥረቴ ምንም የሚሰጠኝ ምንዳ የለም እንዲከፈለኝም አልፈልግም በራሴ ደመወዝ ጥሬ ግሬ የምኖር ኩሩ ዜጋ ነኝ የማንንም ፍርፋሪ መልቀም አልሻም!

ስለዚህ አቤልዬ ምንም የሚከፈለኝ ነገር የለም ሌሎችም አቤልን መሰል ግለሰቦች ይህ ሰው ተከፋይ ሊሆን ይችላል ለዚህ ነው እንዲህ የሚፅፈው ብላችሁ የምትጠረጥሩ ስልትኖሩ ስለምትችሉ ከማንም ምንም የሚፈለኝ ክፍያ እንደሌለ በአደባባይ ላሳውቅ እፈልጋለሁ አንዳንድ ግለሰቦች ስሜት የሚነኩ አስቆጪ ሃሳቦችን ሲሰነዝሩ ተናድጄ ምላሽ የምሰጥበት ሁኔታ ተገቢ እንዳልሆነ አስቤበት ተገንዝቤያለሁ ከእንግዲህ አላደርገውም
የተለያዩ የራሴ ተጨባጭ ምክንያቶች ስላሉኝ የምፅፈው በብዕር ስሜ ነው፤ይህ ደግሞ ችግር ያለው አይመስለኝም፤ጥንትም ሆነ አሁን ዜጎች የሚጠቀሙበት አካሄድ ስለሆነ በብዕር ስሜ የጀመርኩትን ጥረት አጠናከሬ እቀጥላለሁ፤ይህን የማደርገው የማንንም መብት ሳልነካ የራሴንም ሳላስደፍር እንደሆነ እንዲሁም በውድ አገሬ ኢትዮጵያ ላይ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን መታገስ የለብኝም የሚል አቋም አለኝ፤ለብዙሃን ጥሩና ጠቃሚ መልዕክት የሚያስተላልፉ ጉዳዮችን ከማጋራ አልቆጠብም በወዳጅነት አብረን እንቆይ

Post a Comment

0 Comments