ፊንፊኔ #Ethiopia ሚያዝያ 092015(YMN) የሱዳን ሕዝብ የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግስት ወዳጅ ነው፤ባይሆንማ ኖሮ የአገሪቷ መሪዎች በተለያዩ ወቅቶች ነሸጥ ሲያደርጋቸው የሚፈጥሩትን ትንኮሳ አይቃወምም ነበር
ከአንድ አመት በፊት የሱዳን ዜጎች ባካሄዱት የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ኢትዮጵያን እንደሚደግፉና የኢትዮጵያ ወዳጅ መሆናቸውን ሰንድቅ ዓላማችንን በመያዝ ጭምር መፈክር ሲያሰሙ ተመልክተናል
ይህ ደግሞ የአገሪቱ ሕዝብ ለኢትዮጵያ ያለውን ጥልቅ ወዳጅነት የሚያመለክት ነው
አንዳንድ የእኛው መሰሪዎች በዚህ አጋጣሚ ሱዳን በቅርቡ የያዘችብንን መሬት እናስመልስ ሲሉ ሰምቻለሁ ተመልክቻለሁ ይህ ተገቢ አይሆንም ሌላው በችግር ላይ ሲወድቅ ተጨማሪ ችግር መፍጠር አይገባም
እኛን የሚያዋጣን በሕጋዊ መንገድ ብቻ በመጠቀም የተዛባው እንዲታረም ማድረግ ነው፤አሁን ችግር ላይ ወድቀዋልና የእነርሱ ባለስልጣናት ቀደም ሲል ባገኙት አጋጣሚ ወረውናል መሬታችንን ይዘዋል እኛም ብድር እንመልስ ማለት አዋጭ አካሄድ ሊሆን አይችልም ወይም በአጋጣሚው ለመጠቀም የሚፈልግ ኃይል አለ ማለት ነው
ቀደም ሲል በማን አለብኝነት የተንቀሳቀሱ የሱዳን ጀነራሎችና ባለስልጣናት የፈፀሙት ጥፋት እንዲታረም የኢትዮጵያ መንግስት በመስራት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፤የተፈፀመው ሕገ ወጥ ድርጊት ጊዜውን ጠብቆ መታረሙ የማይቀር ነው
አሁን የሱዳን ሕዝብ ችግር ላይ ነው በተለይም የአገሪቷ መዲና ካርቱምና ሌሎች ከተሞች ሰላም እንዳጡ እየተዘገበ ነው ዛሬ በወጡ ዘገባዎች ሶስተኛ ቀኑን በያዘው ወታዳራዊ ግጭት ምክንያት የ97 ሰዎች ሕይወት አልፏል የማቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል ያሳዝናል!
ግጭቱ የተነሳው በሁለት ወታደራዊ ኃይሎች መካከል ነው፤ተቃዋሚ የአገሪቱ ተጣቂዎችና የሽግግር መንግስት ሰራዊት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት የከፋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት በአስቸኳይ እንዲቆም በአለም አቀፍ ተቋማት አመራሮች እየተጠየቀ ነው
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት ሁለቱም የሱዳን ተፋላሚዎች ግጭታቸውን እንዲያቆሙ ጠይቀዋል፤የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሓፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስም ትናንት ባስተላለፉት መልዕክት በሱዳን የተጀመረው ግጭት በአስቸኳይ ይቁም ብለዋል
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባለፈው ቅዳሜ በአረብኛ ቋንቋ ባስተላለፉት መልዕክት ሁለቱ የተጋጩ ወገኖች ግጭትን ከሚያባብስ ድርጊት በመቆጠብ ችግራቸውን በውይይት እንዲፈቱ ጠይቀዋል
ኢትዮጵያ የምትጠቀመው ሱዳን ሰላም ስትሆነ ነው ሰላም ይብዛላት እንላለን በጎረቤት የሚታይ ጭስ እኛንም የሚጎዳ ነው
ሱዳናውያን የመጨረሻ አማራጫቸው ወደ ኢትዮጵያ መሰደድ እንደሚሆን ከዚህ በፊትም ታይቷል፤ይህ ደግሞ በእኛ ላይ የሚፈጥረው ተፅኝኖ አለ 'በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ"ይሆንብናል ስለዚህ ሱዳኖች ሰላም ወርዶ በአገራቸው ውስጥ እንዲኖሩ እንመኝላቸዋለን፤ሱዳን ጎረቤታችን ናት ሰላም እንዲበዛለት እንሻለን!
0 Comments