"ሰገጤ ምን እንደሆነ አላውቅም" ልደቱ አያሌው

 

ፊንፊኔ #Ethiopia ሚያዝያ 01,2015(YMN) ብዙዎች ልደቱ ክህደቱ ይሉታል "ታዋቂው የፖለቲካ ሰው"የሚባለውን አቶ ልደቱ አያሌውን፤ከ1997 ዓ.ም ታሪካዊ ምርጫ በኋላ ቅንጅት በተባለው ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ምክንያት ለመታወቅ ምቹ ሁኔታ ያገኘው አቶ ልደቱ አያሌው አሁን አገር ውስጥ እንደማይኖር ይታወቃል
በለውጡ መጀመሪያ ወራት ላይ "የልብ ህመም አለኝ ወደ ውጭ በመሄድ መታከም አለብኝ" ብሎ በመጠየቅ ከብዙ ጊዜ ንዝንዝና ቆይታ በኋላ ወደ አሜሪካ ለመግባት ዕድሉን አግኝቶ በመሄድ እዚያው የቀረ መሆኑ ቀድሞም በህመም በማሳበብ  ለመውጣት አስቦ ነው እንጂ ልክ እንደ ሃብታሙ አያሌው ወደ ውጭ በመውጣት በመንግስት ላይ ጫና ለመፍጠር ነው ብለው ያሰቡ ብዙዎች  ናቸው
እንደታሰበውም ልደቱ ያሰበውን አድርጓል፤ወደ ውጭ አገር ሄዶ ከተደላደለ በኋላ በለውጡ መንግስት ላይ ጫና ለመፍጠር ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፤ከግብረ አበሮቹ ጋር ከመስከርም 30 በኋላ ሕጋዊ መንግስት የለም በማለት መንግስት ላይ ጫና  ለመፍጠር ሞክሯል አልቻለም ጥረቱ ከንቱ  ሆኖ ቀረበት
ከዚያም በኋላ በተለያዩ የጽንፈኛ ሚዲያዎች ላይ በመቅረብ ትንታኔዎችን በመስጠት ላይ ይገኛል(ትንታኔ ከተባለ) ከሰሞኑም በቤቲ ሾዎ ከቤተልሄም ታፈሰ ጋር አንድ ቆይታ አድርጎ ተመልክቻለሁ(ቤተልሄም ጽንፈኛ አይደለችም)
ልደቱ ከቤቲ ሾዎ ጋር ባደረገው ቆይታ ከሰሞኑ ፖለቲካዊ ሁኔታና በቅርቡ ይፋ ባደረገው ጽሑፍና መጽሓፉ ላይ ትኩረት በማድረግ ተናግሯል ስለእውነት  ቤተልሄም በጥም ጥሩ ጥያቄዎችን አቅርባለታለች
እኔን ባስገረሙኝ ጉዳዮች ላይ ብቻ ላተኩርና አቶ ልደቱ በዚህ ውይይት ላይ"ሰገጤ ማለት ምን ማለት እንደሆነ አላውቅም" ብሏል አራዳ የሚባሉ ሰዎች የሚጠቀሙባቸውን ቃላት ማወቅና መረዳት የማይችል ሰው እንዴት አድርጎ ነው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የሚሳተፈው?  ብዬ ለመጠየቅ ተገድጃለሁ
እኔ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ እንደምረዳው ሰገጤ ማለት የማያውቅ፤የማይረዳ፤ነገር የማይገባው ገገማ ማለት ነው እና አቶ ልደቱ  ቢያንስ  የሰገጤን ትርጉም መረዳት ሳይችል፤ የኢትዮጵያን ፖለቲካና የዕድገት ደረጃ መረዳት የማይችል እንዲያው በጭፍን በደመ ነፍስ የሚጓዝ ነው ማለት ነው፤ሰገጤ የሆነ ሰው በብዙዎች ትግል የመጣውን ለውጥ በመሻር ከመስከረም 30 በኋላ መንግስት የለም በማለት ፎክሯል
ልደቱ ከቤቲ ሾዎ ጋር ባደረገው ቆይታ እንዳለው በለውጡ ሰሞን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ለተደጋጋሚ ጊዜ ከአንድ ሰዓት ተኩል በላይ መወያየቱን መናገሩ ከሰገጤነትም አልፎ ጉረኛነቱን አሳይቷል፤ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ልደቱ ምን ስለሆነ ነው ይህን ያህል ሰዓት በመስጠት ለዚያውም ለተደጋጋሚ ጊዜ ከልደቱ አያሌው ጋር የሚወያዩት? ሰገጤ ምን ማለት እንደሆነ የማያውቅ ሰገጤ አሁንም ሰገጤነቱን  ማቆም አልቻለም
በቅጥረኝነት የለውጡን መንግስት ለመገልበጥ እየተፍጨረጨረ ነው ነገር ግን ሰገጤ ስለሆነ የለውጡን መንግስት መገለበጥ እንደማይችል ሊረዳ ይገባል! ለነገሩ በሰገጤነቱ ምክንያት  ይህን እውነታም መረዳት እንደማይችልም ይታወቃል፤ የሰገጤን ትርጉም ማወቅ ያልቻለ ሰገጤ!አሜሪካ ተቀምጦ መንግስትን ለመገልበጥ ይፍጨረጨራል

Post a Comment

0 Comments