ፊንፊኔ #Ethiopia ሚያዝያ 15,2015(YMN) የፊንፊኔ/አዲስ አበባ ወጣቶች ከሰሞኑ እጅግ በጣም
ጠቃሚ ውይይት ማካሄደቸውን መገንዘብ ተችሏል፤በውይይት መድረኩ ላይ ከተነሱ አስተያየቶች መረዳት እንደተቻለው ውይይቱ በየክፍለ
ከተማዎችም ተካሂዷል በሚሊንየም የስብሰባ አዳራሽ የተካሄደው ውይይት የማጠቃለያ ውይይት እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል
የፊንፊኔ/አዲስ አበባ ከፍተኛ አመራሮች ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር አባይና
የፊንፊኔ ቅርጫፍ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በተገኙበት የሚሊኒየም አዳራሽ የተካሄደው ውይይት በጣም ጠቃሚ
ወጣቱን ኃይል ከብዥታ የሚያወጡ ተጨባጭና ጠንካራ መልዕክቶች ተላልፈዋል
ለወጣቱ ጥያቄዎች በየደረጃው ምላሽ ለመስጠት ምቹ ሁኔታዎች እንዳሉ፤ወጣቱ ከአፍራሽ ኃይሎች ሴራ ራሱን
እንዴት መጠበቅ እንደሚችልና በለውጡ አመራር የተጀመሩ ተስፋ ሰጪ ስራዎችን በራሱ በወጣቱ ተሳትፎም ጭምር እንዴት ማስቀጠል
እንደሚቻል መልዕክት የተላለፈበት ነው
ከየክፍለ ከተማው የተወከሉ ወጣቶች በመድረኩ ላይ
ከየክፍለ ከተማቸውና መኖሪያ አካባቢያቸው ተጨባጭ ሁኔታዎች ተነስተው ያለምንም ስጋትና ፍርሃት የሚሰማቸውን ሃሳብ
አንስተዋል ጥያቄዎችን ጠይቀዋል ከፊንፊኔ አዲስ አበባ ከፍተኛ አመራሮችም እስከ አሁን የተከናወኑ ወጣቱን ተጠቃሚ ማድረግ የቻሉ
የልማትና ዕድገት ስራዎች ላይ ጠቃሚና ተስፋ ሰጪ ምላሾችን አግኝተዋል
እንደሚታወቀው ከወጣቶቹ ጋር በሚሊነየም አዳራሽ የተካሄደው ውይይት ሙሉ ይዘት በመገናኛ ብዙሃነ
ለአድማጭ ተመልካች የቀረበው ትናንት ምሽት ነው ገና ውሎ አላደረም ይህን ውይይት በሚሊየን የሚቆጠሩ የመገናኛ ብዙሃን
ተከታታዮች ገና ይመለከቱታል
ይህን እውነታ የመረዳት አቅም የሌላቸው እነ አቶ ነአምን ዘለቀና መሰሎቹ ከወዲሁ ማናናቅ መጀመራቸውን
ተመልክቻለሁ አንድ ፐርሰንት እንኳ አልተከታተለውም ብሏል መሰሪው ነአምን ዘለቀ ይህን በማለቱ የሚያገኘው የፖለቲካ ጥቅም ምን
እንደሆነ ባይታወቅም ዓላማው ግን ለወጣቶች ጠቃሚ ውይይት ንቀቱን ያሳየበት እንደሆነ መረዳት ተገቢ ነው
በውጭ የተሸሸጉ
እንደዚህ አይነት ሰዎች ለወጣቱ ኃይል ጥቅም መረጋገጥ ጠብ የሚል ነገር ማድረግ የማይችሉ ወሬኛ ናቸው፤አቶ ነአምን እና መሰሎቹ የወጣቶቹ ውይይት ምንም ተመልካች አላገኘም ማለት ለወጣቶች ከማሰብና ከመጨነቅ እንዳልሆነ ወጣቶቹ ይገነዘባሉ ምክንያቱም እንደ እነርሱ ከአገራቸው ተሰደው ሳይሆን በአገራቸው በከተማቸው ውስጥ እየኖሩ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ያውቃሉና ሁሉንም ነገር በምክንያት በማየት የመረዳት ብቃትና ችሎታ አላቸው
በወጣቱ እጅ እሳት መያዝ የሚፈልጉ ኃይሎች ለወጣቱ የተሰጠውን ግልፅና ጠቃሚ ማብራሪያ መኮነናቸው የሚጠበቅ
ነው ምክንያቱም በተለያዩ ምክንያቶች ብዥታ ውስጥ በመግባት የሚከተላቸውን
ወጣት ያጣሉና፤የመብገናቸው ተጨባጭ ምክንያት ይኸው ነው፤ሌላ ምንም ሊሆን እንደማይችል ይታወቃል
በቀጣይም ወጣቱ በራሱ የሚያደርገው ጥንቃቄ እንዳለ ሆኖ አመራሩ ሳይዘገይ አፍራሽ ኃይሎች በየጊዜው በሚፈጥሩት
አጀንዳ ውዥንብርና ብዥታ ውስጥ እንዳይገባ በወቅቱ ማብራሪያ ቢሰጥ መልካም ነው፤ጽንፈኞች በየጊዜው ለሚፈጥሩት አጀንዳ ሁሉ ምላሽ
መስጠት አስፈላጊ ባይሆንም እጅግ ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ግን ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ወጣቱም ሆነ ሌላው የህብረተሰብ ክፍል በቂ
መረጃ እንዲያገኝ ማድረግ ያስፈልጋል
የፊንፊኔ/አዲስ አበባ አመራሮች
አሁን ያከናወኑትን ስራ የሌሎች ክልሎችና ከተሞች አመራሮችም እንደ ልምድ በመውሰድ ወጣቶች በወቅታዊ የአካባቢያቸውና የአገራቸው
ጉዳዮች ላይ ተገቢ መረጃዎችን በወቅቱ ማግኘት እንዲችሉ መሰራት ይጠበቅባቸዋል!
ለምንኛውም እነ እንቶኔ በቀጣይ የፊንፊኔ/አዲስ አበባ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊ ካድሬ ወጣቶችን ነው የሰበሰበው የሚለውን ዲስኩራቸውን የምንሰማ ይሆናል
0 Comments