ፊንፊኔ #Ethiopia ግንቦት
10/2015(YMN) ከ40 በላይ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስሪያ ቤቶች ቢሮዎች፤ ኮሚሽኖች፤ባለስልጣን መስሪያ ቤቶች፤ድርጅቶች፤ኤጄንሲዎች
በፊንፊኔ/አዲሰ አበባ ይገኛሉ
የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ
OBN ሚዲያ ኮምፕሌክሰ በፊንፊኔ/አዲስ አበባ ተገንብቶ ተገባዷል ግዙፉ የሚዲያ ተቋም በቅርቡ ከአዳማ ወደ ፊንፊኔ ይዛወራል ተብሎ
ይጠበቃል ያኔ ፀጉርህን ትነጭ እንደሁ የምናየው ይሆናል
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ዋና መስሪያ ቤት በፊንፊኔ/አዲስ አበባ ተገንብቶ ተገባዷል;የኦሮሞ የባህል ማዕከላት በፊንፊኔ/አዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች ተገንብተዋል
በፊንፊኔ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች የአፋን ኦሮሞን ትምህርት እያስተማሩ ነው
ታዲያ አቶ ታዬ ደንደአ ተቃወመ
ብለህ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ቤተ መንግስት በፊንፊኔ/አዲሰ አበባ መገንባት መጀመሩን የምታጥላላና የምትቃወም አንተ
ማነህ?እኮ ማነህ? ባልደራስ ነህ? ወይስ ፊንፊኔን በረራ ናት እያልክ የምትቃዠው ጽንፈኛ ቡድን ነህ? ውጣ ከፊት ለፊት! ካለህ
አምጣ መረጃና ማስረጃህን! አለበለዚያ ዝም በል!
በመንግስት መዋቅር ውስጥ
የሚገኝ አቶ ታዬ ደንደአ የቤተመንግስቱን ግንባታ ስለተቃወመ ግንባታው የሚቆም የሚመስላቸው ድኩማኖች አሉ አይሆንም፤ሊሆንም አይችልም!ተስፋችሁን
ቁረጡ!
ሌላው ሁሉም የክልል መንግስታት
በየዋና ከተማ መቀመጫቸው ቤተ መንግስት አላቸው፤የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በመቀመጫው ፊንፊኔ ከተማ ላይ ቤተ መንግስት
ቢገነባ የቱ ላይ ነው ስህተቱ?እስከ አሁንም በመዘግየቱ ሊጠየቅ ነው የሚገባው!አዎን ዘግይቷል ከ30 ዓመታት በኋላ መሆኑ እጅግ
በጣም ያስቆጫል!
ሆኖም ከመቅረት መዘግየት
ይሻላልና የቤተመንግስቱን ፊንፊኔ/አዲስ አበባ ላይ መገንባት ጥቂቶች ምክንያት ለቃቅመው ቢቃወሙም ብዙዎች ሚሊዮኖች ኦሮሞዎች ብቻም
ሳይሆኑ ሌሎቹም የኦሮሞ ወዳጅ ወገኖች ሙሉ በሙሉ ይደግፋሉ ተው!ተቃውሞህ ለከት ይኑረው!
የኦሮሞ ሕዝብ ራሱን በራሱ
ማስተዳደር ከጀመረ ከ30 ዓመታት በኋላ የሚያስተዳድረው መንግስት በፊንፊኔ ቤተመንግስቱን መገንባት ጀመረ መባሉ ራሱ እንዴት እንደሚያሳፍር
ማን በነገረህ!ወያኔ የሰራችውን ሴራ ጨምሮ ውስብስብ ምክንያቶች እንዳሉ ይታወቃልና ብዙዎች የመዘግየቱን ምክንያት ይረዳሉ
አሁን ደግሞ ኦሮሞ ያለምንም ስጋትና ጭንቀት ቤተመንግስቱን በፊንፊኔ ላይ ለመገንባት ጊዜው
ሆነ!ተረኛስ ተብሎ የለ?ምን አለበት የተረኝነቱን ጊዜ ተጠቅሞ እንኳ ቤተመንግስቱን ቢገነባበት?አይ ተረኛ! ድንቄም ተረኛ!
0 Comments