ፊንፊኔ #Ethiopia ግንቦት 29/2015 (YMN) በአሜሪካም ሆነ በሌሎች የውጭ አገራት ውስጥ የሚኖሩ አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ወገኖች ስለ አገራቸው መልካም የሚያስቡ፤መልካም የሚመኙና መልካም የሚሰሩ ናቸው
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በቁጥር 2 ሚሊየን 500 ሺህ ናቸው፤ከእነዚህ ውስጥ አብዘኞቹ የሚኖሩት በሰሜን አሜሪካ፤በአውሮፓና በመካከለኛው ምስራቅ አገራት ውስጥ ነው
ከጥቂት ባንዳና ከዳተኞች በስተቀር አብዛኞቹ ስለ ኢትዮጵያ አገራቸው የሚጨነቁና ዘወትር የሚያስቡ ናቸው
ጥቂት ባንዳና ከሃዲዎች ግን የሚሳካላቸው መስሏቸው በቅጥረኝነት አገራቸውን ለማፍረስና ኢትዮጵያ ላይ በውጭ ኃይሎች ማዕቀብ እንዲጣልባት የሚፍጨረጨሩ መሆናቸውን ከሰሞኑ ታዝበናል
በውጭ የሚገኙ ዳያስፖራ ወገኖች ገንዘባቸውን ወደ አገር ቤት በሕጋዊ መንገድ እንዳይልኩ ሕገ ወጡን አካሄድ እንዲጠቀሙ፤ግፊት ማድረግ በሌሎች ላይ ጫና መፍጠር የሚጎዳው መንግስትን ሳይሆን ሕዝብን አገርን ነው፤ እነዚህ ግለሰቦች ይህን እንኳ መገንዘብ የማይችሉ መሃይሞች መሆናቸውን በድርጊታቸው አረጋግጠዋል
የውጭ ምንዛሪ በመቅረቱ ምክንያት የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መንግስት ቅንጣት ታህል የሚጎዳበት ሁኔታ የለም፤ሊኖርም አይችልም መንግስት በእነርሱ ጫጫታና ጫና የሚወድቅበት ሁኔታ ፈፅሞ የለም
ስለዚህ አገራችሁን የምትወዱ ዳያስፖራ ወገኖች የቤተሰቦቻችሁ መመኪያ የሆናችሁ ቅኖች፤ስለ ኢትዮጵያ አገራችሁ ሌት ተቀን የምታስቡ ወገኖች ገንዘባችሁን እንደከዚህ በፊቱ በሕጋዊ መንገድ ለቤተሰቦቻችሁ ላኩ! ይህን ስታደርጉ አገራችሁን ትጠቅማላችሁ አገራችሁ ኢትዮጵያ ስትጠቀም እናንተም በተዘዋዋሪ መንገድ የምትጠቀሙ መሆናችሁን ለእናንተ ማስረዳት አያስፈልግም
እነ ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ፤ነአምን ዘለቀና ሌሎች ጥቂት ጀሌ ትንሾች ሲጮሁ ውለው ቢያድሩ ኢትዮጵያችን ከዕድገትና ብልጽግና ወደ ኋላ ላትመለስ ጉዞዋን ወደፊት አድርጋለች፤ግስጋሴዋን አጠናክራለች፤ማንም ወደ ኋላ ሊመልሳት አይችልም የሚችልበት ሁኔታም የለም
ኢትዮጵያ በየትኛውም ጽንፈኛ ቡድን ጫጫታና መፍጨርጨር ከዕድገት ጉዞዋ ወደ ኋላ የምትመለስበት፤ዕድገትዋ የሚገታበት ሁኔታ አልፏል!ኢግዚአብሔር ይመስገን!
0 Comments