"በባለፈው ጦርነት የተጎዳነው ሁላችንም ነን" - ከንቲባ አዳነች አቤቤ



ፊንፊኔ #Ethiopia ሰኔ 04/2015(YMN) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ ለትግራይ ክልል ከ510 ሚሊየን ብር በላይ የአይነት እና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከሌሎች የከተማው ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በመሆን መቐለ ተገኝተው ነው ያስረከቡት።

ድጋፉ ህዝቡንና በጎ አድራጊዎችን በማስተባበር የተበረከተ ሲሆን ከተደረገው ድጋፍ ከ218 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆነው የጥሬ ገንዘብ ሲሆን እና ቀሪ ደግሞ የተለያዩ ቁሳቁሶች ናቸው።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፤ " ከሰላም እንጂ ከጦርነት ትርፍ ስለማይገኝ ሰላማችንን ማጽናት አለብን " ያሉ ሲሆን " በባለፈው ጦርነት የተጎዳነው ሁላችንም ነን " ብለዋል።


 



" በየትኛው የሀገሪቱ ጫፍ የሚያጋጥም ጉዳት የሁሉም ጉዳት በመሆኑ የወደመውን በትብብር መልሰን እንገነባለን " ሲሉም አሳውቀዋል።

የትግራይ ግዜያዊ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቃል በገባው መሠረት ለትግራይ ክልል ድጋፍ ለማድረግ ቅድሚያ ተነሳሽነቱን ወስዶ ተግባራዊ በማድረጉ ምስጋና አቅርበዋል።

"ተጋግዘን በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች ወደ ልማት እና እድገት መመለስ አለብን" ብለዋል። 

=>መረጃው ከAMN የተገኘ ነው



Post a Comment

0 Comments