“አንድ ብር እንኳ አንሰርቅም’’

 





ፊንፊኔ #Ethiopia ሰኔ 29/2015(YMN) በሌቦች ላይ በቁርጠኝነት የዘመተን መንግስት መጠርጠርና ሌላውም እንዲጠረጥር መንቀሳቀስ ከተጀመረ ሰነባብቷል

ዋነኞቹ አቀንቃኞች በውጭ አገራት የሚኖሩ ናቸው ከውስጥ የሚገኙቱ መልዕክት ተቀብለው የሚያራግቡ ናቸው በውጭ የሚገኘው ባንዳ ከአገር ወስጡ ባንዳ ጋር በመቀናጀት እንደሚሰራ ይታወቃል አለበለዚያማ ነገሩ ጦዞ እንዲህ አይግለበለብም ነበር

ለማንኛውም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከብዙ ጊዜ ትዕግስትና ዝምታ በኋላ ነገርየውን ዛሬ አፍረጥርጠው ይፋ አድርገዋል መልካም ነው ጠርጣራውም እፎይ ይበል!አውቆ አበዶቹም ተስፋቸውን ይቁረጡ!

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሌላ አገር ዜጋ አይደሉም ኢትዮጵያዊ ናቸው፤ለአገራቸው ኢትዮጵያ ልማትና ዕድገት ባላቸው ቁርጠኝነት ምክንያት አያደርጉትም እንጂ ቀደም ሲል የነበሩቱ የአገር መሪዎች አድርገው እንዳለፉት ቢያደርጉት እንኳ መውቀስና በሕግም እንዲጠየቁ ማድረግ ይቻላል

ዶከተር አብይ አህመድ አገር ወደማስተዳደር ሃላፊነት ከመጡ በኋላ በሰሯቸውና ባሰሯቸው የተለያዩ የልማት ስራዎች በሚሊየን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን እጅግ በጣም ደስተኞች ናቸው

በጣት የሚቆጠሩ ጥቂት ምቀኞች ግን በቅናት ተንጨርጭረው ተመልክተናቸዋል!የሁሉም ልማት ፕሮጀክቶች ገንዘብ ምንጭ ከየትና ከእነ ማን እንደተገኘ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አንድ በአንድ ቆጥረው በዝርዝር አስረድተዋል፤መልካም አድርገዋል!

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ማብራሪያቸው ላይ ላይ እንደጠቆሙት ባንዳ ምቀኞቹ የተንጨረጨሩት አይችሉም ብለው ሲለፍፉ ቢቆም ሁሉም ተችሎ በማየታቸው ነው፤ኦሮሞ አገር ማስተዳደር አይችልም ብለው የረጩት የፕሮፓጋንዳ መርዝ አልሰራላቸውም ከሸፈባቸው! ኦሮሞ ከሌሎች እህት ወንድሞቹ ጋር በመሆን አገር ማስተዳደር ብቻ ሳይሆን አገርን እንዴት ማስተዳደርና ማሻገር እንደሚቻልና ለአዲሱ ትውልድም ተጨባጭ የሚታይ ተስፋ ማሳየት ችሏል፤ባንዳዎቹ ፅንፈኞች እንደለመዱት በሃሰት ስም ከማጥፋት ውጭ ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ተረጋግጧል

 

                       

Post a Comment

0 Comments