የባንዳ ልጆች ድግስና ክሽፈታቸው



ፊንፊኔ #Ethiopia ነሃሴ 12/2015(YMN) የባንዳ ልጆች አልተሳካላቸውም ከሽፈዋል፤ያቀዱትና ያለሙት ከግብ ሊደርስላቸው አልቻለም፤መክሸፋቸውን በአደባባይ ላይ በማየት አረጋግጠናል

በብልጽግና ውስጥ የተሰገሰጉ ሰርጎ ገቦች አገር እንድትፈርስ ሲሰሩ የከረሙትን፤ሲሸርቡ የቆዩትን ሴራ በአደባባይ ላይ በከዱ አማካይነት ዘረገፉልን፤አሁን ይፋ የሆነውን ሴራ ስናውቅ ቀደም ሲልም የሃይማኖት ጉዳይን ተገን በማድረግ መንግስትን በአጭር ጊዜ ውስጥ ገልብጠን አራት ኪሎ እንገባለን ሲባል የነበረው ከብልጽግና ውስጥ ያለውን ሰርጎ ገብ በመተማመን እንደሆነ ተረድተናል

ከሰሞኑ አቶ ከዱ በተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ተቀምጦ ዘና ብሎ ለማንበብ የሞከረው ጽሑፍ በባንዳ ልጆች ቅንጅት የተዘጋጀ መሆኑን ኩነቱ አረጋግጦልናል

በአማራ ክልል በሰፊው ሕዝብ የተመረጠ መንግስት ጊዜው ሳይጠናቀቅ በአቋራጭ ስልጣን ለመያዝ ሲባል የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት ተጠየቀ፤በአማራ ክልል ሕግ ለማስከበር የገባው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ይውጣና ወደ ካምፑ ይመለስ ተብሎም በድፍረት ሲጠየቅ ሰማን

የድፍረቱ ምንጭ ምን እንደሆነ መገመት አይከብድም፤ቦሃ ዕቃው ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ ከጽንፈኛ ዳያስፖራ የባንዳ ልጆች የሰበሰበው ዶላር መጠን ከፍ ያለ መሆኑ፤ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶችም በቂና አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርጉ በማረጋገጣቸው ምክንያት እንደሆነ ይታወቃል

የድግሱ ቅድመ ዝግጅት ከፍ ያለ ነው፤ሰንሰለቱ ከፊንፊኔ እስከ ካይሮና ምዕራባዊያን አገራት የተዘረጋ መሆኑን ተግባራቻው አረጋግጦልናል፤አሁን ወደ ለቅሶ ደረጃ ላይ ከመደረሱ በፊት ቀደም ሲል ሲሳማ የነበረው ቀረርቶና ፉከራ ዋነኛ መሰረት በሁሉም ደረጃ የተደረገው ቅድመ ዝግጅት እንደሆነ አሁን ግልጽ ሆኗል

በተዘረጋው ሰንሰለት ውስጥ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በግልጽ የሳይበር ውጊያውን እየተዋጉ ካሉ ግለሰቦች በተጨማሪ በአገር ውስጥ በመንግስትና በግል የሚዲያ ተቋማት ውስጥም ተዘጋጅተው የሚጠባበቁ ጃውሳዎች እንዳሉ ይታወቃል

ነገር ግን የታቀደው ሁሉ ተግባራዊ ሊሆንላቸው አልቻለም፤እንዳሰቡት መንግስት አልተገለበጠም የክሽፈታቸው ዋነኛ መሰረት ይህ ነው፤ከሰሞኑ እንደተደረገው በሚዲያዎች ውስጥ የሚገኙ የባንዳ ልጆች ሰንሰለት ውስጥ የገቡ ሰዎች የተሰጣቸውን የቤት ስራ ለመወጣት የተለያዩ መረጃዎችን በመስጠት ግዴታቸውን እንደሚወጡ ይታወቃል ከእንግዲህ ምንም ቢያደርጉ አይሳካላቸውም!

ወያኔ ቀደም ሲል ለ30 ዓመታት ኢትዮጵያን በጉልበት ስታስተዳድር የገነባችውን አቅምና የኢትዮጵያን ጠላቶች ድጋፍ በመተማመን ነው የተሽመደመደችበትን ጦርነት የጀመረችው፤የጃውሳ አለቆችም መተማመኛቸው የውጭ አቅምና በአገር ውስጥ የተፈጠረው ሁኔታ እንደሆነ ግልጽ ነው

የጃውሳው ኃይል የወያኔን ያህል በጦርነት ውስጠ መቆየት አይችልም!ምክንያቱም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀደም ሲል በሚታሰበው ደረጃ ላይ የሚገኝ አይደለም፤አድጓል ተመንድጓል፤የሕዝቡ ግንዛቤም አድጓል አሁን አገሩ እንትፈርስ ለአሸባሪ ቡድኖች የሚያደርገው ፍጋፍ አይኖርም፤ከመረጠው መንግስት ጋር ተቀናጅቶ አገሩን ከአፍራሾች እንደሚጠብቅ በተግባር አሳይቷል

ታሪካዊ ጠላቶቻቸን ይህን እውነት ስለሚያውቁ ተላላኪዎችን ይጠቀማሉ እንጂ በፊት ለፊት መጥተው መዋጋት አይችሉም

እንደለመዱት ከፍተኛ በጀት በመመደብና የጦር መሳሪያ ድጋፍ በማድረግ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ጥረት ያደርጋሉ፤ኢትዮጵያን ማፍረስ እንደማይችሉ ለተደጋጋሚ ጊዜ አይተው አረጋግጠዋል

የባንዳ ልጆች ዘንደሮ ያላሰሙት ዲስኩር የለም፤ፊንፊኔን ጨምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ከተሞችን አማራ ነው የመሰረተው፤የአባቶቻችንን ታሪክ እናድሳለን በማለትም ፈገግ አሰኝተውናል

ለማንኛውም ቀደም ሲል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የአማራ ሸኔና የኦሮሞ ሸኔ መኖራቸውን በሰጡት መረጃ በይፋ ሲያረጋግጡ የጮሃችሁና ያጉረመረማችሁ ግለሰቦች አሁን እንዴት ነው ገብቷችኋል?ለማንኛውም ሁለቱም ሸኔዎች የባንዳ ልጆች ናቸው!የተሰጣቸውን ተልዕኮ ከግብ ማድረስ ያልቻሉ ክሹፎች መሆናቸው ተረጋግጧል፤ታላቋ ኢትዮጵያ አሸንፋለች!

Post a Comment

0 Comments