በፈጣሪ ቸርነት 2015ን አልፈን ወደ አዲሱ ዘመን ደርሰናል። ኢትዮጵያ በውጣ ውረድ ውስጥ እያሸነፈች ተጉዛለች።
የተሳኩልን ሁሉ የኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን ውጤቶች ናቸው። የተፈተንባቸው ደግሞ በመለያየት የተነሣ የመጡ ናቸው። በቀጣዩ ዓመት ፈተናዎቻችን እጅግ ቀንሰው፤ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ከአልማዝ ጠንክሮ፤ የኢትዮጵያን ሰላምና ደኅንነት በጽኑ መሠረት ላይ እናጸናዋለን።
ልማትና ብልጽግናዋን ወደሚመጥናት ደረጃ እናሻግረዋለን።
አዲሱ ዓመት የኢትዮጵያ ብልጽግና ዓመት እንዲሆን እመኛለሁ።
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ጳጉሜን 6 ቀን 2015 ዓ.ም
0 Comments