ፊንፊኔ #Ethiopia መስከረም 01/2016(YMN) ፊንፊኔ/አዲስ አበባ ለሁላችንም የምትመች የጋራ ቤታችን ሆና እንድትገነባ በጋራ መሥራት ይኖርብናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር "ኅብር አዲስ" በሚል መሪ ሃሳብ የጳጉሜን ቀናት ማጠቃለያና የአዲሱ ዓመት ብስራት የበዓል ዝግጅት በአዲስ ዓመት ዋዜማ አካሂዷል።
ዓመቱ በተለይም የከተማዋ ነዋሪዎች የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች ምላሽ የተሰጠበትና ላጋጠሙ ችግሮች ደግሞ ሁነኛ የጋራ መፍትሄ የተሰጠበት መሆኑን ነው ያነሱት።
የከተማዋን ሰላም ለማረጋገጥ የመዲናዋ ነዋሪዎች ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመሆን የሰሩት ሥራም ውጤት የተገኘበት መሆኑንም ጠቁመዋል።
በከተማዋ የተሰሩ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች የዜጎችን ህይወት በመቀየር ትልቅ አስተዋጽኦ እንደነበረው ተናግረዋል።
መዲናዋ የቱሪስት መናኸሪያ ለማድረግ በተለይም የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማስፋት የተሰራው ሥራም ውጤታማ ነበር ብለዋል።
በአዲሱ ዓመትም እነዚህን ሥኬታማ ሥራዎች ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
አዲሱ ዓመት አዲስ ተስፋ የምንሰንቅበት፣ አዳዲስ ውጥኖችን ለማሳካት በጋራ የምንሰራበት መሆኑን አለበት ሲሉ መግለጻቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በአዲሱ ዓመት እንቅፋቶችን በጋራ ከፊታችን እያነሳን፣ አዲስ አበባን ለሁላችንም የምትመች የጋራ ቤታችን ሆና አንድትገነባ በጋራ መሥራት ይኖርብናል ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
0 Comments