ፊንፊኔ #Ethiopia መስከረም 01/2016(YMN) “በሰው እጅ እሳት መያዝ አይከብድም” ይባላል በዚህ እውነት ምክንያት አንዳንዶች ታዋቂነትና ተሰሚነታቸውን በመጠቀም በማያገባቸው እየገቡ ብዙዎችን ለጉዳት አጋልጠዋል፤የሰዎች ሕይወት እንዲጠፋ አድርገዋል የብዙዎችም አካል እንዲጎድል የበኩላቸውን ድርሻ አበርክተዋል
ከዚህ በፊት ሆኖ በተግባር ያየነው የተመለከትነው ይኸው እውነት ነው፤ በታዋቂ ሰዎች ንግግር ምክንያት
ብዙዎች ተነሳስተው ራሳቸውን ለጉዳት አጋልጠዋል ሞተዋል ቆስለዋል የእንግልት ኑሮ ለመግፋት ተገደዋል
ከመጋረጃው በስተጀርባ የሚቀሰቅሱቱ የሚያነሳሱቱ ግን ከዳር ቆመው እሳቱን ከመሞቅ አልፈው በይፋ ወጥተው
አደባባይ ላይ በአንደበታቸው እንደሚናገሩት ሲሞቱና ሲታሰሩ እስከ አሁን አልተመለከትንም፤ልክ በውጭ አገራት ውስጥ እየኖሩ እንደ
ቁራ እየጮሁ እንደሚውሉት ቅጥረኛ ዩቱበሮች!
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ በአገልግሎታቸው ክብርን የተጎናፀፉ በሃይማኖታዊ
አገልግሎታቸው በፈጣሪ ቸርነት አንቱ ለመባል ዕድል ያገኙ እነዚህ አባቶች አቡነ ጴጥሮስና አቡነ አብረሃም ተከብረው የኖሩትን
ያህል አሁን በመጨረሻው ደረጃ ላይ ውርደት ለመከናነብ ራሳቸውን ያዘጋጁ ይመስለኛል
የሐይማኖት አባቶች ተከታይ ምዕመናንን ለማነሳሳት ሲባል እንዲህ ይናገራሉ ብዬ አልጠበኩም ጠብቄም አላውቅም በግለሰብ የእኔ አመለካከትና የግንዛቤ ደረጃ እንዳለ ሆኖ ሌሎች ወገኖችም ከእነዚህ የሓይማኖት አባቶች እንደዚህ ዓይነት ጫፍ የወጣ ንግግር ያሰማሉ ብለው እንደማያምኑ እገምታለሁ
እነዚህ አባቶች በአዲስ ዓመት 2016 ዓ.ም ዋዜማ በሰጡት መግለጫ “ዓይናችን እያየ ዝም ማለት
አንችልም፤ከሚታሰሩት ጋር አብሮ ለመታሰር፤ከሚሞቱት ጋር አብሮ ለመሞት ራስን ከማዘጋጀት ውጭ ሌላ እድልና ምርጫ አይኖረንም”
ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል
በእርግጥ ይህን መሰል ጥሪና ተከታዮችን ማነሳሳት ሙከራ ቀደም ሲልም ለተደጋጋሚ ጊዜ ተሰምቷል፤ ጥሪው
የተለያዩ የሃይማኖት ተከታዮች እንዲጋጩ እልቂት እንዲፈጠር በአጋጣሚውም በአቋራጭ ስልጣን መያዝ የሚፈልጉ ቡድኖች እንዲጠቀሙ
ለማድረግ ታስቦ ሆን ተብሎ ታቅዶና በበቂ ቅድመ ዝግጅት የሚደረግ ጥሪ መሆኑን ከተደጋጋሚው የሴራ ድርጊት መረዳት የሚከብድ
አይሆንም
ኢትዮጵያ ውስጥ የብሔርና የሐይማኖት ግጭቶችን ተገን በማድረግ ወደ ስልጣን ኮርቻ ፊጥ የማለቱ ጊዜ
አልፎበታል፤ዘመኑ አይፈቅድም ዜጎችም እሺ አይሉም በብሔርና በሐይማኖት ግጭቶች በመጠቀም የመንግስትን ስልጣን ያለ ምርጫ
በአቋራጭ መያዝ እንደማይቻል እስከ አሁን መረዳት አልቻሉም ማለት ነው?እነዚህ ኃይሎች ቆሞ ቀሮች ሆነዋል የሚባለው ከኋላ ቀር
ድጊታቸው በመነሳት እንደሆነ ግልጽ ነው
ጽንፈኛ ኃይሎች የውስጥና የውጭ የኢትዮጵያችን ጠላቶች መንግስትን በተለያዩ በሚታወቁ ችግሮች ምክንያት
አዳክመው በመጨረሽም የሚጎመዡለትን ስልጣን ለመቆናጠጥ የተጀመረው ጥረት የተለያዩ ተላላኪዎችን በመጠቀም የቀጠለ
ይመስላል፤ባለፈው የካቲት ወር 2015 የአድዋ ድል ክብረ በዓልን ተገን ለማድረግ ግርግር በመፍጠር አራት ኪሎ ለመግባት ከፍተኛ
ጥረት ተደርጎ ከሽፎባቸዋል፤የካቲት 5ና 23 2015 ዓ.ም በፊንፊኔ የተሞከረውን ማስታወስ ይገባል!
ከውጭም ሆነ ከውስጥ ያሉ ጽንፈኛ ኃይሎች በአቋራጭ አራት ኪሎ መግባት እንደማይቻል ሲረዱ ወደ አማራ ክልል
በመሄድ ጦርነት ከፍተው ጀግናውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በመድፈራቸው ምክንያት እየከፈሉ ያሉት ዋጋ አገር ያወቀው ፀሐይ
የሞቀው እውነት ሆኗል
ይህም ሙከራ አለመሳካቱ ሲረጋገጥ አሁን ለተደጋጋሚ ጊዜ የሞከሯትን የሐይማኖት ግጭት ለመፍጠር ጥረት የተጀመረ
መሆኑን ከእነዚህ የሃይማኖት አባቶቹ የተልዕኮ መልዕክት ማረጋገጫ ነው፤እነዚህ የሃይማኖት አባቶች የአሁኑን ጥሪ ያሰሙት
የአማራን ብሔር ተገን በማድረግ ነው
“መልዕክታቸው በቂም በቀልነት አማራ እየታሰረ ነው እየሞተ ነው ለምን ዝም ትላላችሁ? ተነሱ እንጂ”የሚል
ነው በሐይማኖት አባትነታቸውም የእምነቱን ተከታዮች እያነሳሱ እንደሆነ ግልጽ ነው፤ስለዚህ እነዚህም ካባ የለበሱ ፅንፈኞች ናቸው፤ተልዕኮ ተቀብሎ በድፍረት ፊት ለፊት ከወጣው የጃውሳ ቡድን የሚለዩ አይደሉም አካፋን አካፋ ብሎ በስሙ መጥራት ግድ ነው!
እንዲያውም የክፋቱና የጥፋቱ ሁሉ የላይኛው ምሽግ መሆናቸውም አሁን ግልጽ ሆኗል።ሲፈልጉ የኃይማኖት ካርድን ሲፈልጉ የብሔር ተበዳይነት ቂም በቀል ሰይፍን የሚመዙ መሆናቸው ይኸው በተግብር ታይቷል።
በእኩይ ተግባራቸው ምክንያት ከቤተክህነት እየተነጠሉ ወደ መጨረሻው የውድቀት ደረጃቸው የደረሱ ይመስለኛል።ህዝብንና አገርን ይዘው እንዳይጠፉ ጥንቃቄና ትዕግስት ያስፈልጋል።
በተለይም እንደለመዱት በመጪዎቹ ሳምንታትና ወራት በአደባባይ ላይ የሚከበሩ
መስቀልና ሌሎች ሐይማኖታዊ በዓላትን ለግጭት መቀስቀሻ ለመጠቀም በቂ ቅድመ ዝግጅት ያደረጉ ይመስላሉ
ስለዚህ ወገን ሆይ ነቃ በል! በመጨረሻው ጊዜ መንግስት እንደሆን መንግስት
ነው በጉልበት የመጣበትን ኃይል ያለውን ጉልበት ተጠቅሞ መመከቱ የማይቀር ይሆናል፤መብቱም እንደሆነ ይታወቃል!አዲሱ ዓመት
2016 ዓ.ም የሰላም የጤና እና አሳሳች መልዕክት ከሚያስተላልፉ ህገ ወጦች ራሳችንን የምንጠብቅበት ይሁንልን!
0 Comments