ከንቱ ፍጡር ለወገኑ የማሰብ ሞራል የለውም!


በ150 ሺህ ብር ራሱን የሚሸጥ ፍጡር!ባንዳ! ለሕዝብ ግድ የለውም ብዙሃን ቢጎዱ ጉዳዩ አይደለም ቅጥረኞች ማሰብ የሚችሉት ስለ ጥቅማቸው ብቻ እንደሆነ በታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ ትናንት የተሞከረው የሽብር ድርጊት ሌላ አካባቢ አይሞከርም ብሎ ማሰብ ተገቢ አይሆንም

ጽንፈኛው ኃይል ከፍተኛ የተስፋ መቁረጥ አበሳ ውስጥ ገብቷል በውጭ የሚገኘው ጽንፈኛ ቡድን በገንዘቡ ኃይል ብቻ የሚፈልገውን ሁሉ ማድረግ እንደሚችል ያስባል

ተስፋ የቆረጠ ኃይል ለአገር ቀጣይነት ማሰብ የሚያስችል ሞራል ሊኖረው አይችልም ተስፋ ቆራጭ በአጥፍቶ መጥፋት የሽብር ተግባር ውስጥ ከመግባትም ወደ ኋላ አይልም

ስለዚህ በቀጣዮቹ ሕዝባዊ በዓላት ብርቱ ጥንቃቄና እጅግ በጣም ጠንካራ ቁጥጥር ማድረግ ያስፈልጋል በተለይም ጽንፈኞች በደረሰባቸው ኪሳራ ምክንያት ፊንፊኔና ሌሎች ዋና ዋና አካባቢዎች ላይ በሚከበሩ ታላቅ የደመራና ኢሬቻ በዓላት ላይ የሽብር ድርጊታቸውን በመፈፀም ተሰሚነትና ተቀባይነት ለማግኘት ሙከራ ሊያደርጉ እንደሚችሉ መጠርጠር ይገባል

ሐይማኖታዊና ሕዝባዊ በዓላትን በመጠቀም በአገርና ሕዝብ ላይ ጉዳት  ከማድረስ ወደ ኋላ የማይል ከንቱ ፍጡር መኖሩን ልብ ብለን አካባቢያችንን ቀዬአችንን የስራ ቦታችንን  መከታተልና መጠበቅ ግዴታ ነው!ከሕዝብ ተሳትፎ ውጭ የፀጥታ ኃይሎች ብቻቸውን ምንም ማድረግ አይችሉም! ወገን ነቃ እንበል!

በንዝህላልነት ዝም ካልንስ ምን ይሆናል ብለን እንጠይቅ! አሁን ያለው ሁኔታ የእኔ ጉዳይ አይደለም እኔን ምን አገባኝ አገር የሚያስተዳድር መንግስት ይወጣው የራሱ ጉዳይ ብለህ በተለመደው የምን አገባኝ በሽታ ውስጥ ከሆን ዞሮ ዞሮ ችግሩ በመምጣት ቤትህ ይደርሳል፤ከዚያ ቅጥረኛ ተላላኪዎች ወሮበላው የሚፈጽመው ድርጊት ስፍር ቁጥር ሊኖረው አይችልም

ሁሉም ከተበላለሸ  ተነስተህ ያኔ እንዲህ ባደረኩ ኖሮ እያልክ ብትቆጭ ምንም የምታመጣው ለውጥ አይኖርም፤ጠላት አገር ካፈረሰ በሁዋላ ምንም ማድረግ የምትችለው ነገር የለም፤ስለዚህ አስከፊው ጥፋትና ጉዳት ከመድረሱ በፊት ጠንከር ብሎ መስራት መንቀሳቀስ አስፈላጊ ነው


Post a Comment

0 Comments