ከአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መምሪያ ዕዝ የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ ቁጥር 5
መስከረም16 እና 17 የሚከበሩት የመውሊድ፣ የደመራና የመስቀል በዓላት በአማራ ክልል የሃይማኖቶቹ ሥርዓት በሚፈቅዱት መንገድ እንዲከበሩ ኮማንድ ፖስቱ እየሠራ ነው።
የሕዝብ ስብሰባዎች በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ መከልከላቸው ይታወቃል። ይሄም ጽንፈኛና ዘራፊ ኃይሎች በሕዝብ ላይ ሊያደርሱት የሚችሉትን ጉዳት ለመቀነስ ታስቦ የተደረገ ነው።
መስከረም 16ና 17 የሚከበሩት ሃይማኖታዊ በዓላት የአደባባይ በዓላት በመሆናቸው ለበዓላቱ ሥነ ሥርዓት ሲባል የአደባባይ መሰባሰብን መፍቀድ አስፈልጓል።
በመሆኑም የሚከተሉት ትእዛዛት እንዲፈጸሙ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መምሪያ ዕዝ ያስታውቃል፦
2. የአደባባይ መሰባሰቦች የበዓላቱ አከባበር ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ብቻ የሚከናወኑ ናቸው።
3. በእነዚህ አከባበሮች ወቅት ለሕዝብ ደኅንነት ሲባል ከጸጥታ አካላት ጋር መተባበር ግዴታ ነው።
መስከረም 14 ቀን 2016
የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መምሪያ ዕዝ
0 Comments