በዓላቱ በሰላም ተከብረው ማለፋቸውን የጋራ ግብረ ኃይሉ አስታውቋል




ፊንፊኔ #Ethiopia መስከረም 16/2016(YMN) በዛሬው ዕለት በመላው ሀገራችን የተከበሩት የመስቀል ደመራ እና የመውሊድ በዓላት በሰላም መጠናቀቃቸውን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታወቀ።

የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ቅደመ ዝግጅት በማድረግ በዕቅድ እየተመራ ተጋላጭ ቦታዎችንና አካባቢዎችን ለይቶ በቅድመ መከላከል ሥራው ላይ በርካታ የሰው ኃይል በማሰማራት እና ለሥራው አጋዥ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ከህዝቡ፣ ከሁለቱ የእምነት ተቋማት የሃይማኖት አባቶች፣ ከበዓላቱ አዘጋጅ ኮሚቴዎችና ከወጣቶች ጋር ተባብሮ በመስራቱ በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች ሁለቱም በዓላት በሰላም መጠናቀቃቸውን አስታውቋል፡፡

በዓላቱ በሰላም እንዲጠናቀቁ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረገው ህዝባችን እንዲሁም የሐይማኖት አባቶች፣ ለበዓሉ አስተባባሪ ኮሚቴዎች እና ለወጣቶች የጋራ ግብረ ኃይሉ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርቧል።

ህብረተሰቡ እንደተለመደው የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ እያሳየ ያለውን ቀና ትብብር ወደፊት በሚከበሩ ሌሎች ህዝባዊና ሐይማኖታዊ በዓላት ላይም አጠናክሮ እንዲቀጥል የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ- ኃይሉ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

Post a Comment

0 Comments