ፊንፊኔ #Ethiopia
ጥቅምት 04/2016(YMN) ከሰሞኑ የትግራይ ወገኖቻችን
ሃዘን ተቀምጠዋል ፈጣሪ ጽናቱን ይስጣችሁ እንላለን!ይህን ብለን ግን ዝም አንልም እውነት እውነቱን እንነጋገራለን፤እንቅጯን
ስናወጋ በእናንተ ላይ ብቻ ሳይሆን በጥጋበኞችና ትዕቢተኞች አነሳሽነት ምክንያት በሁላችንም ላይ የደረሰው አስከፊ ችግር ዳግም
እንዳይመጣ ማድረግ እንችላለን
ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ
በትግራይ ለሁለት ዓመታት የዘለቀው ጦርነት የጎዳው ትግራይን ብቻ ሳይሆን መላውን ኢትዮጵያ ነው ማለት ይቻላል በእርግጥ ዋናው
ጦርነት በትግራይ ክልል ምድር ላይ የተካሄደ ስለሆነ በትግራይ የደረሰው መከራና እንግልት ከሌሎቹ ጋር ሊነፃፀር የሚችል
አይደለም
ዋናው ጉዳይ ይህን መከራና
እንግልት የጋበዘው ማነው እርሱ?የሚለው ነው እውነቱን ግልጥልጥ በማድረግ መነጋገር ግዴታ ነው “አለባብሰው ቢያርሱ በአረም
ይመለሱ”እንዲሉ እንዲያው ሸፋፍነን ካለፍነው መልካም አይሆንም
የሕወሃት ቁንጮዎች እፍረት
የሌለባቸው! ከትግራይ እናቶች ፊት ለፊት መቆም የቻሉት ነገሩ ሁሉ”የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም” ሆኖባቸው ይመስለኛል
ውድ የትግራይ ወጣቶችን በማነሳሳት
ወደ እሳት የከተተውና ለአሁኑ ሃዘን የዳረገን ጽንፈኛው የትግራይ ዳያስፖራና የሕወሃት ባለስልጣናት ቅንጅት መሆኑን ለአፍታም
መዘንጋት አይገባም!
የትግራይ ዳያስፖራ ከውጭ
ጠላቶች ጋር በፈጠረው ጠንካራ ግንኙነት ምክንያት አለም አቀፍ ተቋማት የተሳሳተ መረጃ እንዲያገኙ በማድረግ እንደ አገር
ኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዲፈጥሩ ማድረግ ችሏል፤በዚህ ረገድ ተሳክቶለታል ማለት ይቻላል፤ዳያስፖራው በውጭ አገራት
የአስፋልት መንገድ ላይ በመንከባለልም እውነት ያለው መስሎ ቀርቧል
በዚህና ሌሎች ተያያዥ
ምክንያቶች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ለ13 ጊዜ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ብቻ ተወያይቷል፤ተጽዕኖ
ለመፍጠር ሞክሯል፤ይህም በታሪክ ተመዝግቧል፤አሜሪካም በማን አለብኝነት ኢትዮጵያ ላይ የተለያዩ ጉዳት አድራሽ ማዕቀቦችን ጥላለች፤ዓለም
አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ባላቸው አቅም ሁሉ ኢትዮጵያ ላይ በመዝመት ሰርተዋል
የትግራይ እናቶች ድምፂ
ወያኔን ብቻ እንዲከታተሉ ስለተደረገና የኢንተርኔት ግንኙነትም ለረጅም ጊዜ ተዘግቶ በመቆየቱ ምክንያት በወቅቱ ስለ ጦርነቱ
ሂደትና ጉዳት በቂ መረጃ ይኖራቸዋል ተብሎ አይታሰብም
የወያኔ ቁንጮዎች በስልጣን
ዘመናቸው የሁሉም ፈጣሪ አድራጊ ስለነበሩ በደነደነ ልባቸው “ጦርነት ባህላዊ ጨዋታችን ነው” ብለው በሕዝብ እንቢተኝነትና ትግል
ለመልቀቅ የተገደዱትን ስልጣን ዳግም ለማግኘት በመቋመጣቸው ምክንያት ጊዜ ያለፈበትን የጦርነት ስልት በመጠቀም እንደ ሕዝብ
መላውን የትግራይ ክልል ነዋሪ ቀሰቀሱ አነሳሱ፤ጦርነቱ ሕዝባዊ ነው
በቀጥታ አዲስ አበባ ነው የምንገባው ብለው ለወጣቱ `ሃይል ያልተገባ ቃል በመግባት በድፍረት እንዲነሳሳ
አደረጉት፤ወጣቶች ያለምንም ስጋት እንዲንቀሳቀሱ አደንዛዥ ዕጽ እንዲጠቀሙ ጭምር ማድረጋቸው በወቅቱ ይፋ በተደረጉ መረጃዎች
ተረጋግጧል
የትግራይ እናቶች በውዴታና ግዴታ ውድ ልጆቻችሁ ተነጠቁ፤ይህ ነው የሚባል ጥቅም ለማይገኝበት ጦርነት ተማገዱ የደረሰው ጉዳት ይታወቃል፤በመጨረሻም የሕወሃት ቁንጮዎችም "ህወሃትና የትግራይ ህዝብ አንድ" ነው ብለው እንዳልፎከሩ "አብይ አህመድን እስከ ሞያሌ ድረስ እንከተለዋለን አንለቀውም ማንም አያድነውም" ብለው ሲያቅራሩና ሲፎክሩ ቢቆዩም በፍፃሜው ልካቸውን አውቀው አይሆኑ መሆናቸውን ስለተረዱ ወደ ፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ለመሄድ ተገደዱ
ጦርነቱ በሰላም ስምምነት
መጠናቀቁ መልካም ነው የትግራይ እናቶች ልጆች ሊመለሱ ባይችሉም እፎይታ ተገኝቷል፤በጦርነቱ ምክንያት የተፈጠረው ምስቅልቅል ግን
እስከ አሁንም መፍትሄ ያገኘ ስላልሆነ የትግራይ እናቶች የሕይወት ፍላጎታችሁ ሁሉ ተሟልቶ ተመችቷችሁ እየኖራችሁ እንዳልሆነ
ሁሉም ወገናችሁ ይረዳል
ዋናው ጉዳይ ያለፈውን
ማሳላሰል አይደለም ወሳኙ የወደፊቱ ነው ትውልድ ይቀጥላል የሕይወት እንቅስቃሴ ለአፍታም አይቆምም ስለወደፊቱ ማሰብና የሰላም
ስምምነቱ በተማላ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆን የትግራይ ክልል ነዋሪዎችና መላው የክልሉ ተወላጆች ያላቸው ሚና የማይተካ ነው
ስምምነቱ ሳይሸራረፍ ተግባራዊ
ሆኖ የቀድሞው አኗኗር እንዲመለስ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዲጠናከር ማድረግ ያስፈልጋል የክልሉ ጊዜያዊ የሽግግር መንግስት
የሁሉንም ድጋፍ ይሻል፤በተለይም የትግራይ ተወላጆች ዳር ቆመው ከመመልከት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ማደረግ ይጠበቅባቸዋል
የትግራይ ምሁራን፤ባለሃብቶችና
ሌሎች አቅም ያላቸው ወገኖች ሁሉ ትግራይ እንድታገግም ከወደቀችበት እንድትነሳ የሚችሉትን ድጋፍ ሁሉ ማድረግ አለባቸው፤ይህ
በተግባር ሲታይ ሌላው ወገንም ዝም ይላል ተብሎ አይጠበቅም
አሁንም በተቃራኒው መንገድ
የሚሄዱ አገረ ትግራይ፤ትግራይ አገር መሆን አለባት!የሚሉና ጎረቤት አገር ኤርትራን በፕሮፓጋንዳቸው የሚተነኩሱ በኢትዮጵያና
ኤርትራ መካከል የምናውቀው አስከፊ ጦርነት እንዲነሳ የሚንቀሳቀሱ አፍራሽ ፕሮፓጋንዳ የሚነዙ፤ሩቅ ላይ ሆነው እሳት በመሞቅ
የራሳቸውን ገቢ የሚያደልቡ ወገኖች ስላሉ እነዚህን እረፉ ማለትና ልካቸውን አውቀው አደብ እንዲገዙ ማድረግ ያስፈልጋል!ኢትዮጵያ
ትስዕር!
0 Comments