የምን ባንዲራ? ሰንደቅ ዓላማ ነው እንጂ!



ፊንፊኔ #Ethiopia ጥቅምት 05/2016(YMN) ባንዲራ ምንድነው?ባንዲራ አትበሉ ተብለናል ትዕዛዙን በማክበር ተግባራዊ ማድረግ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ግዴታ ነው
“ትክክለኛው አጠራር ሰንደቅ ዓላማ ነው ባንዲራ የባዕድ ቋንቋ ነው”ብለዋል ክብርት የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
ክብርት ፕሬዚደንታችን ያስተላለፉትን ትክክለኛ መልዕክት ከልብ በመቀበል ከአሁን በኋላ ባንዲራን የእነ ሶላቶን ቋንቋ እርግፍ አድርገን በመተው ሰንደቅ ዓላማ የሚለውን ስያሜ ጠበቅ አድርገን እንያዛት!
ምን ጎድሎን በባዕድ ቋንቋ ሙጭጭ ብለን እንቀራለን?የራሳችን ይሻለናል!የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀን ለ15 ዓመታት በተከታታይነት በየዓመቱ ሲከበር አንድም ሰው ስለዚህ ጉዳይ ሲናገር አልሰማሁም
ይኸው በ16ኛው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀን ክብረ በዓል ላይ ባሰሙት ንግግር ክብርት ፕሬዚደንታችን ሳህለወርቅ ዘውዴ ሹክ አሉን እናመሰግናለን ፕሬዚዳንታችን በጣም እንወድዎታለን!ዕድሜና ጤና ይስጥልን!🇪🇹🇪🇹🇪🇹



Post a Comment

0 Comments