የባህር በር ባለቤትነት አነጋጋሪው ዋና አገራዊ አጀንዳችን!



ፊንፊኔ #Ethiopia ጥቅምት 10/2016(YMN) የሰሞኑ ዋነኛ አገራዊ አጀንዳችን የባህር በር መሆኑን የማይረዳ የለም ሊባል ይችላል፤ከሊቅ እስከ ደቂቅ ትንሹም ትልቁም ስለ ቀይ ባህርና የባህር በር ጉዳይ ሲያወራ ሲጥል ሲያነሳ መመልከትና መስማት ተዘውትሯል

በጉዳዩ ላይ ምሁራን ገንቢ ትንታኔዎችን በመስጠት ላይ ይገኛሉ፤መሃል ሰፋሪዎችና ጽንፈኞች እንዳሉ ሆነው፤ አልፎ አልፎ የታሪክ አዋቂዎችም የጥንት የጠዋቱን አንስተው ትውስታቸውን በማጋራት ላይ ይገኛሉ፤እጅግ በጣም መልካም ሁኔታ ነው ያለው፤መልካሙን ሁኔታ፤አስደሳቹን ተስፋ እየተመለከትን ነው

የሰላሙ ሎሬት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ የባህር በር ጉዳይ ላይ ለተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሰጡት ማብራሪያ በይፋ በመገናኛ ብዙሃን ከተሰራጨ ወዲህ ምን እየተባለ ነው?ብለን ብንጠይቅ ምላሹ  ብዙ ነው

በተለይም ጉዳዩን በመቃወም ከቆሙ ወገኖች እየተሰማ ያለው ሁሉ፤ሁሉንም አገር ወዳድ ዜጎች በቁጭት በማነሳሳት የለውጡን መንግስት እንዲደግፉ የሚያደርግ መሆኑ ተረጋግጧል “ላለው ይጨመርለታል”

ብልጽግና መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት የቀይ ባህርና የባህር በር ባለቤትነትን ጉዳይ በዚህ ወቅት ለሕዝብ ውይይት ይፋ ማድረጉ ለብልፅግናም መልካም ነገርን ይዞለት መጥቷል በማለት በድፍረት መናገር የሚቻልበት ሁኔታ ተፈጥሯል

ሁኔታው “እንኳን ዘንቦብሽ እንዲያውም ጤዛ ነሽ” ያስብላል፤ቀደም ሲል ከ14 ሚሊየን በላይ አባላት ማፍራት የቻለው የብልጽግና ፓርቲ የቀይ ባህርና የባህር በር ባለቤትነትን ጉዳይ በማንሳቱ ብቻ የአባላቱ ቁጥር በእጥፍ ይጨምራል ወይም ከዚህ በላይም ሊሆን ይችላል፤ይህ ለምን ሆነ ማለት አይቻልም ምክንያቱም ጉዳዩ የአገር ጉዳይ፤ የኢትዮጵያ ጉዳይ ነዋ!

በዚህ የሚበሳጭ ካለ ምንም ማድረግ አይቻልም ብለን እናልፋለን፤ማን ከጎታቾች ጋር ይቆማል?ጉዞ ወደፊት ነው እንጂ!

በአገር ውስጥ መንግስትን ከስልጣን አወርዳለሁ ብሎ ያለ አቅሙ የተንቀሳቀሰው ኃይል አቅሙን አይውቅምና የኢትዮጵያን የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ለማጣጣል የባጥ የቆጡን በመነካካት ተፍጨርጭሯል ያልተገባ ሙከራ ማድረጉ ተስተውሏልል፤ያው ሙከራው ከንቱ ሙከራ  እንደሆነ ይታወቃል በውጭ የሚገኘው የጽንፈኛው ኃይል ደጋፊ ቡድንም ቀደም ሲል ለዘመናት በባህር በር አስፈላጊነት ላይ ምን ሲል እንደኖረ የማይታወቅ ይመስል በሚታወቅበት ክህደት ምክንያት በኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ሃሳብ ላይ ለመሳለቅ ሞክሯል፤ሁኔታው ከኤርትራ ድጋፍ ያስገኝልኛል ብሎ በማሰቡም የኤርትራ ወዳጅ ሆኖ መቅረቡን ተመልክተናል

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የመሸገው የጽንፈኛው ኃይል ሰራዊት ነጋ ጠባ የሚያዘንበው ስድብ፤ዛቻና ማንቋሸሽ ስፍር ቁጥር የሌለው ሆኖ ቀጥሏል፤ኢትዮጵያ እንደ አገር” ትለብሰው የለ ትከናነበው አማራት” ተብላለች ይህ ያስገርማል የበሉበትን ወጪት ሰባሪዎችንም ለመፋለም ያስገድዳል

እነዚህ ኃይሎች በቅጥረኝነት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ ስለሆኑ የቅጥረኝነት ግባቸው እንዲሳካ ታላቋን አገር ኢትዮጵያን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ተጠቅመው ከማዋረድና ከማፍረስ ወደ ሁዋላ እንደማይሉ እሙን ሆኗል፤ጽንፈኞቹ ጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ እያለ የቀጣሪዎቻቸውን ተልዕኮ ማሳከት እንደማይችሉ ይታወቃል

ወደ ዋናው አገራዊ አጀንዳችን ስመለስ ኢትዮጵያችን ሩቅ ሳይሆን በቅርቡ የባህር በር ባለቤት በመሆን ተጠቃሚነቷን ታረጋግጣለች፤ይህን ለማስቀረት የሚችል ምድራዊ ኃይል የለም ብለን መናገር የምንችልበት ሁኔታ ተፈጥሯል

ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ጎረቤት አገራት ፍላጎታቸውን እንዳንፀባረቁ በመነገር ላይ ይገኛል፤ጉዳዩ እየተብላላ ቆይቶ የመጨረሻው ውጤት በኢትዮጵያ መንግስት የሚወሰን ይሆናል፤በእርግጥ ከተለያዩ የጎረቤት አገራት በቀረበው ሃሳብና ጥሪ ላይ ኢትዮጵያ ምንም ያለችው ነገር ባይኖርም በዕቅዷ መሰረት ጉዳዩን እንደምታጤነው ይታወቃል

በሌላ በኩል የኤርትራ መንግስት በዚህ ሳምንት ባስተላለፈው መልዕክት “የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግስታት ምንም ጉዳይ ባላነሱበት ሁኔታ ላይ የሚሰጠው አስተያየት ትክክል አይደለም ጉዳዩ የሚመለከታችሁ ሁሉ ጥንቃቄ አድርጉ” ብሏል መልካም ነው

የጎረቤት አገረ ኤርትራ መንግስት ይህን ገንቢ መልዕክት ቢያስተላልፍም መንግስታቸው ለሰጠው ማሳሰቢያ ክብር የሌላቸው አንዳንድ የኤርትራ ተወላጆች አክቲቪስቶችና የወያኔ ደጋፊዎች የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄና አጀንዳ የማጣጣል ዘመቻ መክፈታቸው ይታወቃል፤እነዚህ ጎታቾች ናቸው ትክክል ካልሆነው አካሄዳቸው የማይቆጠቡ ከሆነ ተጎጂ የሚሆኑት እነርሱ ናቸው እንጂ ታላቋ ኢትዮጵያ አይደለችም!

 

 

 

Post a Comment

0 Comments