ፊንፊኔ #Ethiopia ጥቅምት
12/2016(YMN) ጉልበት ሲኖርህ፤አቅም አለኝ ብለህ ስታስብ የሌላው ጉዳይ አይገድህም ስለ ሌላው ጉዳትና እንግልት ምን ቦጣህና
ታስባለህ?ጭንቀቱና መንገላታቱ የራሳቸው ይሁንላቸው!
የምዕራባዊያን አገራት የጉልበተኞቹ
ሁኔታ እንዲህ ነው፤እነርሱ ስለ ሌላው ግድ የሌላቸው መሆናቸውን ለተደጋጋሚ ጊዜ በተግባር አሳይተውናል፤በኢትዮጵያችን ላይ በማን አለብኝነት
ቀደም ሲል የፈፀሙትንና አሁንም ያልተውትን በደል ስለምናውቅ የእነዚህ ጉልበተኞች ጉዳይ መቼም ቢሆን ያሳስበናል
ምዕራባዊያን ኢትዮጵያ ቀና እንዳትል
ምን ያልሰሩት ያልከወኑት ነገር አለ?አሁንስ ምን እያደረጉ ነው?ጉዳዩን በጥሞና መመርመርና ማየት ለራስ ይጠቅማል፤ጉልበተኞቹ መተማመኛቸው
ገንዘብና ጉልበታቸው ነውና በጉልበታቸውና ገንዘባቸው ተማምነው የለመዱትን በደል ከማድረስ ወደ ኋላ አይሉም፤ቀደም ሲል ሁሉንም በማን
አለብኝነት አድርገዋል ወደፊትም ያደርጋሉ
እንደሚታወቀው ሁል ጊዜ የሚንገበገቡለት
የራሳቸው ብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ ስለሚያስገድዳቸው ያዝ ለቀቅ እያደረጉ ነው እንጂ እነርሱኮ እስከነ አካቴው ብንጠፋላቸው ደስታቸው
ወደር የለውም፤ዋናው ፍላጎታቸው የተፈጥሮ ሃብቶቻችንን መዝረፍና መቀማት ስለሆነ በየትኛውም ሁኔታ አቅመ ደካማ መሆናችንን አጥብቀው
ይሻሉ
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኢትዮጵያ
ተገዳዳሪ መንግስት ማግኘት ስለቻለች በቅርቡ በተካሄደው የሰሜን ጦርነት ወቅት ተረባርበው ይህን ሞጋችና ተገዳዳሪ መንግስት ድምጥማጡን
ሊያጠፉ ብዙ ለፍተዋል፤ጥረው ግረው ያደረጉትና ለተላላኪያቸው የመደቡት በጀት ሁሉ ዶጋመድ ሆኖ ቀረባቸው እንጂ እኛ ዛሬ በምንገኝበት
ሁኔታ መገኘት አንችልም ነበር
የኢትዮጵያ ሕዝብ የመረጠውን መንግስት
ደግፎ በአንድነት ቆሞ እንቢ በማለቱ ምክንያት የምናውቃቸው ምዕራባዊያን አገራት በተላላኪዎቻቸው ተጠቅመው ሊያጠፉን አልቻሉም፤ተዘጋጅተው
በመጡበት ልክ እኛም ተዘጋጅተን ህብረታችንን አጠናክረን ተገዳደርናቸዋ!
ከሁለት ዓመታት በፊት ለተላላኪያቸው
ወያኔ ምን ያላደረጉት ድጋፍ አለ?በወቅቱ ለነበሩ የወያኔ ታጣቂዎች ከቴክኖሎጂ ድጋፍ ጀምሮ ኃይል የሚሰጠውን ምግብ ተጠቅመው እስከ
መላክ መድረሳቸውን አውቀናል፤በወቅቱ እውነቱ ሲነገር “ወይ ጉድ”ብለን ነው ተገርመን ያለፍነው
ምዕራባዊያን ይህን የመሰሪነትና
በሴራ የታጀበ እኩይ ድርጊታቸውን የሚያከናውኑት በእርዳታ ድርጅቶቻቸው አማካኝነት እንደሆነ ከተረዳን ሰንብተናል፤የድርጅቶቻቸው ዋነኛ
ተግባር እርዳታና ድጋፍ ማድረግ እንዳልሆነ ይታወቃል የእርዳታና ድጋፍ ጉዳይ ሽፋን እንደሆነ ሁሉም ከተገነዘበው ቆይቷል
ከሰሞኑ ደግሞ ዋና ትኩረታቸው ፍልስጤሞች
ላይ መሆኑን ስንመለከት በእኛ ላይ ያደረሱትና የፈፀሙት ሁሉ ትዝ ይለናል፤እንዴትስ ልንዘነጋው እንችላለን?አሸባሪ ነው ብለው በፈረጁት
የሃማስ ቡድን ጥቃት ምክንያት እነዚህ የዓለም ጉልበተኞች በፍልስጤም ሕፃናትና እናቶች ላይ እየደረሰ ያለው መከራና መንገላታት ያስደስታቸው
ይሆን?ለመሆኑ ጭካኔያቸው እስከ ምን ድረስ ነው?
እውነት ነው እስራኤል ራሷን የመከላከል
መብት አላት፤እንደማንኛውም አገር የደረሰባትን ጥቃት መከላከል ትችላለች፤ግን ምዕራባዊያን አጋሮቿ አሁን ምን እያደረጉ ነው?የምዕራባዊያን
አገራት አመራሮች ከሰሞኑ ተንጋግተው ወደ ቴልአቪቭ ለምን ሄዱ?መቼም በፍልስጤም ሕፃናትና እናቶች ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት አስደንግጧቸው
ነው ሊባል አይችልም!
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት እስራኤል በጦርነቱ
ራሷን መከላከል እንድትችል የ14 ቢሊየን ዶላር የበጀት ረቂቅ እንዲጸድቅላቸው ለአሜሪካ ኮንግረንስ ለማቅረብ መዘጋጀታቸው ሲሰማ
ተቻኩለው ወደ እስራኤል የተጓዙበትን ምክንያት ምንነት መገመት የሚከብድ አይደለም
ምዕራባዊያን በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ
አገራትን ለማውደም የሚጣደፉ መሆናቸው ሲታወስ የሶማሊያ፤ኢራቅ፤ሶሪያ፤የመን እና የአፍጋኒስታን ሕዝብ ላይ የደረሰው ጉዳት ሊዘነጋ
የሚችል አይደለም
ሳዳም ሁሴን ኒውኩለር ታጥቋል ብለው
ኢራቅን በማን አለብኝነት ጦርነት ካወደሙ በኋላ ይቅርታ መጠየቃቸው አይዘነጋም፤የልባቸውን ካደረሱ በኋላ
ይቅርታ መጠየቃቸው ምንም ትርጉም የለውም፤ በሌሎች አገራት ላይም በተመሳሳይ ሁኔታ ጉዳት አድርሰው ይቀርታ መጠየቃቸው ለጦርነት
እሳት ለተለበለበ ሕዝብ ምንም ጥቅም አያመጣም
ከሰሞኑ ቴል አቪቭ ተገኝተው መክረው ከተመለሱ በኋላ እስራኤል የምድር ጦሯን እንቅስቃሴ እንድታዘገይ
መጠየቃቸው ተሰምቷል፤ይህን ሃሳብ ለእስራኤል ማቅረባቸውን በሚዲያዎቻቸው ይፋ ያደረጉት ከዓለም የሙስሊም ህብረተሰብ
የሚደርስባቸውን ውግዘትና ጫና ለመቀነስ ይመስላል፤እንጂማ እነርሱን የንፁሃን ደም መፍሰስና ሕይወት መጥፋት መቼም
አያሳዝናቸውም!ምክንያቱ ደግሞ እነርሱ ለራሳቸው ካልሆነ ለሌላው ግድ የላቸውም ምን ቦጣቸውና?
0 Comments