ፊንፊኔ #Ethiopia ጥቅምት 25/2016(YMN) እዝቅኤል ገቢሳና ዳዊት ወልደጊዮርጊስ የሚባሉ የትውልድ ዕዳዎች ሰሞኑን አፋቸውን ሲከፍቱ አዳመጥኳቸው። በስማቸው ወይም ቆምንለት በሚሉት ህዝብ እንጂ በአስተሳሰባቸው የአንድ ጎራ ሰዎች ናቸው።
ሁለቱም በጥላቻ የተበከሉ አገር አጥፊና እልቂት ናፋቂ ናቸው።እዝቅኤል ጋቢሳ በፅንፈኛ የኦሮሞ ብሔረተኝነት የሚታወቅ ሲሆን ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ደግሞ ኦሮሙማን(ኦሮሞነትን)ደምስሸ አራት ኪሎ በመግባት ኢትዮጵያን በአማራ አምሳል እፈጥራለሁ የሚልና በአማራ ህዝብ ስም የሚምል የዘመኑ ቁሞ ቀር ባንዳ ነው።እውነት ለመናገር ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ስለሚባል በዕድሜም በአስተሳሰብም የጃጀ ከሀዲ ሰው ማውራት ክብረነክ ነው።
በዚህ
የዕድሜ
ማምሻ
"በአማራ
ህዝብ
ነፃ
አውጭነት
"ስም
በአማራ
ህዝብ
ደም
የሚነግድ
የባንዳ
ልጅ
ባንዳ
ነው።ሰሞኑን
በአንድ
ቦታ
እሱን
መሰል
ቁሞቀሮችን
ሰብስቦ
ሲያነጋግር
አንድ
ተሳታፊ
አንድ
ጥያቄ
አቀረበለት።
"ለመሆኑ
እናንተ
ራሳችሁን
የአማራ
ኃይል...የፋኖ
መሪ
ነን
የምትሉት
ሰዎች
የፖለቲካ
ፍኖተ ካርታችሁ
ምንድነው"የሚል
ጥያቄ።በቁጣ
ጠያቂውን
ያዋከበበትና
ያንጓጠጠበት
መንገድ
በሀፍረት
አንገት
የሚያስደፋ
ነበር።ከዚያም
አልፎ"የኛ
ፍኖተ
ካርታ
መነሻችን
አማራ
መድረሻችን
ኢትዮጵያ
ነው"ብሎ
አጨብጫቢዎቹን
አሳቀቀ።ምን
እንደሚያወራና
ስለምን
እንደሚያወራ
ለመረዳት
ዳቢሎስን
መሆን
ይጠይቃል።
አስገራሚው ነገር የእዝቅኤል ገቢሳ መግለጫ ነው።ይህ ግለሰብ የለውጡ መንግስት ስልጣን በያዘ ሰሞን ከአውሮፓና ከአሜሪካ ተንጋግቶ ወደ አገር ቤት ከገባው ስልጣንና ጥቅም ናፋቂ መንጋ አንዱ ነበር።እዝቅኤል ገቢሳ ከሌሎች ጎልቶ የሚታወቅበት አንዱ በአማራ ህዝብ ላይ ያለው የከረመ ጥላቻና ለትህነግ/ህወኃት ያለው ፍቅር ነው።
እዝቅኤል ገቢሳ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ የለውጡን መንግስት አቅጣጫ ለማሳትና በፍቅር የወደቀለትን ትህነግን ከወደቀበት ለማንሳት ያላደረገው ጥረት የለም።ከመሰሎቹ ጋር በመሆን ለበርካታ ጊዜ ወደመቀሌ ተመላልሶ በኢትዮጵያ ላይ ሴራ አቡክቶ በመጋገር የድርሻውን ተወጥቷል።የለውጡን መንግስት አምርሮ የጠላበት ምክንያትም "የአብይ መንግስት የአማራ ነፍጠኛና አሀዳዊ ስርዓት አስጠባቂ ነው"በሚል እንደሆነ ማንም ያውቃል።
ትህነግ/ህወኃት በሰሜን ዕዝ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ላይ የጭካኔና የሀገር ክህደት ጥቃት በፈፀመበት÷ከዚያም አልፎ አማራንና አፋርን በመውረር የጭካኔ ጭፍጨፋና ውድመት ሲያደርስ ከትህነግ/ህወኃት የዲጂታል ቡድን ጋር በመቀላቀል ለኢትዮጵያ መፍረስና ለአማራ ህዝብ እልቂት የሚችለውን ሁሉ አድርጓል።ከነእስታሊን ገብረስላሴና አሉላ ሰለሞን ጋር በመሆን በኢትዮጵያና በመከላከያ ኃይሏ ላይ÷በአማራ ህዝብና በፋኖ ላይም ያካሄደው የጥላቻና የዕልቂት ቅስቀሳ መቼም የሚረሳ አይደለም።
"የነፍጠኛና አሀዳዊ ስርዓት አስቀጣይ ነው" የሚለው የኢትዮጵያ መንግስት እንዲፈርስ÷አማራም ተዳክሞ የትህነግ ጥቃት ሰለባ እንዲሆን ሁሉንም አቅሙን የተጠቀመው እዝቅኤል ገቢሳ ፍላጎቱ በትህነግና በኦነግ ሸኔ በኩል እንደማይሳካ ሲያረጋግጥ ዛሬ ቆዳውን ገልብጦ ራሱን "ፋኖ "ብሎ የሚጠራው ዘራፊ ሽፍታ ደጋፊና የነዳዊት ወልደጊዮርጊስ መካሪ ሆኖ ቀርቧል።
እጅግ አስተዛዛቢ ከሆነው ንግግሩ "የኦነግ ሠራዊት ተብሎ የሚጠራው መከላከያ ፋኖን ማሸነፍ አይችልም"ሲል ሰማሁት!!ዘራፊውን ቡድን አጀግናለሁ ብሎ ቆምኩለት የሚለውን የኦሮሞ ህዝብ በክህደት አዋርዷል÷የኦሮሞን ህዝብ ለራሱ የከሀዲነት ፍላጎት ማሳኪያ የሚያደርገው መሆኑንም አረጋግጧል።በሌላ በኩል ከእዝቅኤል ገቢሳ ኢትዮጵያ ስትፈራርስና የአማራ ህዝብም ሲኮስስ ከመመልከት የከረመ ፍላጎት አንፃር "የፋኖ"ደጋፊ ሆኖ መቅረቡ ላያስገርም ይችላል።
ምክንያቱም ኢትዮጵያንና መንግስቷን የሚያፈርስለት÷የአማራ ህዝብ ደም እንዲፈስም ነውጥ ከሚያስነሳለት ማንም ጋር መጠጋትና ማገዝ አለበት።ትናንት በትህነግና በሸኔ ያልተሳካው ምኞቱ ዛሬ የአማራን ህዝብ ደም የሚያፈሰው ነፍሰ ገዳይ ቡድን ያሳካዋል ብሎ መጠጋቱ የሚጠበቅ ነው።ለነገሩ በአማራ ነፃ አውጭነት ስም የአማራን ደም የሚያፈሰውን ዘራፊ ቡድን ወደመደገፍ የተሸጋገረው እዝቅኤል ገቢሳ ብቻ አይደለም።
የትናንት የፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-አማራ ፕሮፓጋንዳ ባልንጀሮቹ እነአሉላ ሰለሞን÷ስታሊን ገብረስላሴ÷ቴዎድሮስ ፀጋዬና ሌሎችም የ"ፋኖ"ፕሮፓጋንዳ ሠፈር ተቀላቅለዋል።አዎ!ኢትዮጵያ የምትባል ጥንታዊት አገርና ኢትዮጵያዊ የሚባል ጠንካራ ህዝብ እንዳይኖር የሚፈልጉ ጠላቶች ሁሉ ድሮም ዘንድሮም እንዲህ ነበሩ÷ናቸውም።
ኢትዮጵያን እስከጎዳ ድረስ ከሰይጣንም ጋር አብሮ ማደር።ነገር ግን ምንም እንኳ እዝቅኤል ገቢሳ ከነግሳንግሱ÷አሉላ ሰለሞን ከነኮተቱ የአማራን ምድርና የአማራን ህዝብ የኢትዮጵያ ማፍረሻ ኳስ ሜዳ ለማድረግ ቢሞክርም ህዝብን የማፋጀት ጉጉቱ እንደተናንቱ ሁሉ መምከኑ አይቀርም።
(ዓለምነው አበበ)
0 Comments