የእነ እንቶኔ መፍጨርጨር ያለ ምክንያት አይደለም!






ፊንፊኔ #Ethiopa ጥቅምት 30/2016(YMN) እነ ቢቢሲ፤ቪኦኤና ሌሎችም ታዋቂ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ስለ እኛ በጎ ነገር ማውራት አይሹም በፍፁም! ስለ አፍሪካ መልካም ነገር መዘገብ የሚታሰብ አይደለም
ከሰሞኑ ኢትዮጵያ የባህር በር ያስፈልገኛል ብላ ያቀረበችውን ትልቅ አገራዊ አጀንዳ በበጎ ሊያዩት አልፈቀዱም ምን ቦጣቸውና!
እነርሱን የሚያስደስታቸው ባካበቱት የጋዜጠኝነት ሙያ ተጠቅመው የጌቶቻቸውን አቅጣጫ ተቀብለው ጉድፍ እየፈለጉ እኛን ማብጠልጠል ነው
ደሞኮ አያፍሩም አይናውጣዎች ናቸው፤ጋዜጠኛ ገለልተኛ ነው እውነትን ብቻ ይዘግባል ይሉናል ይህን የሚያስተምሩንን ነገር በተግባር መች አሳዩና!
ድንቄም ገለልተኛ!የውሸት ገለልተኛ መሆናቸውንማ ብዙ ጊዜ ተመልክተናል
ኢትዮጵያ ስለ አነሳችው የባህር በር አጀንዳ አንድም መልካም ነገር ሳይዘግቡ አጀንዳው በአካባቢው ጦርነትን የሚያስነሳ ነው ብለው የሃሰት ዘገባቸውን በማሽጎድጎል ላይ ይገኛሉ
እነዚህን ቱልቱላዎች መመከት ይገባል እነርሱ ለብሔራዊ ጥቅማቸው መከበር ሲቆሙ የአገራችን የዘርፉ ባለሙያዎች ዝም ማለት የለባቸውም፤ባለው አቅም ሁሉ መመከት ይጠበቅባቸዋል፤የሚዲያው ጦርነትም ሊመከት ይገባል
አለበሊዚያ ይህቺኑ ያገኘናትን በነፃነት የመስራት መብት በወሮበሎች ልንነጠቅ እንደምንችል በመረዳት በጉዳዩ ላይ ምሁራን የዘርፉ አዋቂዎች እንዲናገሩና ጉዳዩን ከአገር ብሔራዊ ጥቅም መከበር አንፃር እንዲተነትኑ ዕድል መስጠት ያስፈልጋል
አሁን አገርን በማስተዳደር ላይ የሚገኘውን ብልጽግና ብትቃወም፤ስታብጠለጥል ውለህ ብታድር የምታገኘው ምንም ጥቅም የለም፤በቃ ብልጽግና በህዝብ እውቅና ተሰጥቶት በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ አገራዊ ፓርቲ ነው የተሻለ ፓርቲ ሲመጣ ሳይወድ በግድ የሚለቅ ፓርቲ ነው ብልጽግና!ኢትዮጵያችን ግን የጋራችን ናት የማትቀያየር!
ስለዚህ አታንቀላፋ ስለ ኢትዮጵያ ብለህ ስራ! ጠላትን ተከላከል እንደሌሎቹ ስለ ብሔራዊ ጥቅምህ መከበር ጠንከር ብለህ መስራት ካልቻልክ እመነኝ አንተም መኖር አትችልም፤ምክንያቱም እነ እንቶኔ በመፍጨርጨር ላይ የሚገኙት ሁሉም መኖር የማይችልበትን ሁኔታ ለመፍጠር ነው

Post a Comment

0 Comments