የጉድ አገር




ፊንፊኔ ታህሳስ 17/2016(YMN) የውትድርና ሙያም ሆነ ወታደራዊ አመራር ከሌላው ሙያና አመራር የተለየ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ወታደራዊ ጠበብት ‘’ የውትድርና ሙያን የተቀላቀልክበት ቀን ግለሰብ መሆንህን ያቆምክበት ቀን ነው ‘’(The day you join the military is the day you stop being individual)ይሉታል፡፡በዚህ ምክንያትም ወትድርና እንደማንኛውም የሙያ ዘርፍ ስራ ሳይሆን በራሱ ወታደራዊ ባህልና ማህበራዊ ስርዓት የሚመራ የህይወት መንገድ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡(The military is not just another job, it’s a way of life with its own culture and social order.)ልዩቱን ለመጥቀስ ያህል የውትድርና ሙያ የራሱ ቋንቋ፣ባህልና የንግግር ዘይቤ አለው፡፡በዕለት ከለት ኑሮው፣ወታደራዊ ስልጠናው፣በውጊያ ወቅት የግዳጅ አፈጻጸሙ…የተለየ ነው፡፡ውትድርና ማንም ሰው በቀላሉ የማይረዳው የራሱ ወታደራዊ ዕሴቶችና የዲሲፕሊን መርሆዎች አሉት፡፡የወታደርን ቋንቋ የሚረዳው፣ባህልና ጨዋነቱን የሚገነዘበው፣ወታደራዊ እሴቶቹንና የዲሲፕሊን መርሆዎቹን ልብ የሚለው፤የኃላፊነት ደረጃውን የሚለካውና የግዳጁን ከባድነት የሚመዝነው ቢያንስ ሀገሩን የሚወድና ለመከላከያ ሰራዊቱ ክብር ያለው መሆን ይገባዋል፡፡

በሌላ አባባል ወታደራዊ ሙያ ከሌላው ሙያ የተለየ ሳይንስም ጥበብም ነው፡፡የቴክኖሎጂ መወለጃና ማደጊያ ወታደራዊ ቤት መሆኑን ካልተረዳህ የዕውቀት ችግር አለብህ ማለት ነው፡፡ዛሬ ጠፈሩን የሚያስሰው፣ዓለምን በአንድ መንደርነት የሚያገናኘው ቴክኖሎጂ መወለጃው ወታደር ቤት ነው፡፡ሁሉም ሙያ ወታደር ቤት የከተሙ ናቸው፡፡
ወታደራዊ የአመራር ጥበብንና የአመራር ብቃትን ለመረዳት ደግሞ የበለጠ ከባድ ነው፡፡በአሜሪካ ሰራዊት የውጊያ ኮልጅ (United States Army War College) ድረገጽ ላይ የሰፈረ አንድ ጽሁፍ የወታደራዊ አመራረን ውስብስብነትና የሰራዊት ጀነራሎችን ብቃት እንዲህ ሲል ያብራራል፡፡’’የዘመናዊው አዛዥ የተዋሃደ ታላቅ ሙያዊ ብቃት፣ ግላዊ ዲሲፕሊን፣ ተነሳሽነት፣ ፈጠራ እና የማህበራዊ፣ መንፈሳዊ እና ትምህርታዊ ችሎታዎች እና ልምድ ለወታደሮች እና ለፍላጎታቸው ስሜታዊነት ያለው ጥምረት ሊኖረው ይገባል። በተጨማሪም ፣ የትናንሽ ዩኒቶች እና ትላልቅ አደረጃጀቶችን የውጊያ ዝግጁነት ከፍ ለማድረግ ያለው ተግዳሮት ፣ የቅርብ ጊዜ መሳሪያዎችን እና መሳሪያዎችን ከመቆጣጠር ጋር ፣ የተዋሃዱ የጦር መሣሪያዎችን መዋጋት መርሆዎችን እና የደረጃ-እና-ፋይል ሰራተኞችን በማዘጋጀት የጥራት ማሻሻያዎችን ይጠይቃል ። በተመሳሳይ መልኩ ከፍተኛ መንፈሳዊ፣ ሞራላዊ እና ድርጅታዊ ብቃቶችን የሚያሳዩ መኮንኖች፣ በተለይም የተዋሃዱ አዛዦች ናቸው። አዛዡ በስራ እና በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ለሁሉም ሰው ምሳሌ መሆን አለበት::’’(Successful senior leadership in any institution, including the military, depends on attributes that differ markedly from the skills needed in middle management. "Generalship" is perhaps the most important thing about military leaders, the aspect of our leadership which should make us uniquely valuable to our institution and to the nation. Duty as a general is different from what goes before. Flag officers are more visible; subordinates can defer and waffle because of one's rank and not necessarily stand on the quality of one's ideas. The elements of decisions made at the senior level are more abstract. One often receives conflicting guidance. One usually has less personal control over events. And in spite of all that, senior leaders are more fully accountable and more personally so for results than they were in their duties as more junior officers.)
በአጭሩ ወታደራዊ ሙያና ወታደራዊ አመራር ማንም የፖለቲካ ነጋዴና ማህበራዊ አንቂ ነኝ ባይ የዩቲዩብ ተጧሪ መንደርተኛ ኩታራ እንኳንስ ሊተቸው ቀርቶ ሊረዳውም የሚችል አይደለም፡፡ውትድርና አካላዊና ስነልቦናው ጥንካሬን የሚጠይቅ፣ራስን ለሀገርና ለወገን አሳልፎ የመስጠትን ውሳኔ ያዘለ፣ሰብአዊነት መለያው የሆነ፣የሁሉም ሙያ መነሻ የሆነ ነው፡፡(Intellect,Energy,Selflessness,Humanity,The complete package)በአጠቃላይ ከከፍተኛው እስከዝቅተኛው ያለው ወታደራዊ አመራር ሰራዊት ማሰልጠን፣ማደራጀት፣የውጊያና አገርን የመጠበቅ ብቃቱን ማረጋገጥና በውጊያ ወቅት ድል የማድረግ ሞራላዊና ስነልቦናዊ ብቀቱን የማሳደግ፣ውጊያ ከተነሳም ድል ማድረግን መቻልን የሚመለከት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡
የጦር መሪ ለመሆን ዘመናዊውን የውትድርና ሙያና የቴክኖሎጂ እድገት የሚዋጅ የወታደራዊ መሪነት ስልጠናና ትምህርት ማግኘት የግድ ነው፡፤ወታደር እንዳንተና እንደኔ አንገቱን እያቅለሰለሰ የሚናገር፤ቃላት እየቀደደ የሚሰፋ አይደለም፡፡ንግግሩ ቀጥተኛ ነው፡፡ለዚህ ነው የወታደር ቋንቋ ማወቅ ግድ የሚለው፡፡
በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ ጠባቂና አለኝታ የሆነው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ብቃት በቃል ሳይሆን በተግባር ተደጋግሞ የተረጋገጠ፣ ወታደራዊ አመራሩም በዘመናዊ የውጊያ ጥበብና ስትራቴጂያዊ አመራር የተራቀቀ መሆኑን ለመረዳት የተወጣቸውን ግዳጆች፣ያሸነፋቸውን ጦርነቶችና የውጭ ጠላቶቻችን ሳይቀሩ ከማናቸውም ትንኮሳ የመታቀባቸውን ምክንያት ለሚያጤን ሰው ግልጽ ነው፡፡
ወታደራዊ መሪነት በተለይም ጀኔራል መኮንነት በአካዳሚክስ አውቀትና በዘመናዊ የውጊያ ጥበብና ወታደራዊ አመራር፣በወስብስብ ወታደራዊ ግዳጅ አፈጸጸም ብቃትን በማስመስከር እንጂ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተጥዶ በደም በመነገድ እንደማይገኝ ማንም ሰው መገመት ይችላል፡፡
ከምንም ዕውቀት የጸዱ ጽንፈኞችና ኢትዮጵያ እንድትፈርስ ሰራዊትን ማፍረስ በሚል ክህደት ሰራዊታችንንና የጀኔራል አዛዦቹን ክብር የሚያዋርዱ ከሀዲዎች የሚያካሂዱት ነውረኛ ፕሮፓጋንዳና የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ የሚያሳፍር ነው፡፡አንድም የወታደራዊ ሙያ ግንዛቤ ሳይኖራቸው፣የወታደራዊ አመራርን ጥበብና ብቃት መለኪያ ሚዛን ሳይጨብጡ የሚያካሂዱት አስተዛዛቢ ዘመቻ አንገት ያስደፋል፡፡እነዚህ የፖለቲካ ነጋዴዎችና የዩቲዩብ ጡረተኞች ቢያንስ ህወኃት የተባለ አገር አፍራሽ ቡድን በከፍተኛ ሁኔታ ተደራጅቶና የውጊያ ልምድ ባላቸው ጀኔራሎቹ ተመርቶ በውጭ ድጋፍ ጭምር ታግዞ በሰራዊታችን ላይ የከፈተው ጦርነት እንዴት እንደከሸፈና ለዛሬው ውድቀት እንደተዳረገ እውነቱን ማጤን አይፈልጉም፡፡
እውነትን ፈልጎ ከመረዳት ይልቅ የሰፈር ወሮበላ ታጣቂን በማጀገንና ሰራዊታችንን በማጥላላት ማትረፍን መርጠዋል፡፡አገሩ መቸም የጉድ አገር ነውና ጉደኛው የማህበራዊ ሚዲያ መንጋ የየመንደሩን ማይም ታጣቂ ገፋፍቶ በማስፈጀት ማትረፍን ቀጥሎበታል፡፡ነገ ቢያንስ በታሪክ ተጠያቂ መሆኑ ግን አይቀርም፡፡

በዓለምነው አበበ

 

Post a Comment

0 Comments