ቡና ጋባዡ ጀዋር መሐመድ በተጠባቂው ቃለ መጠይቅ ላይ




ፊንፊኔ ታህሳስ 23/2016(2016(YMN) ነጠላ ትርክቶችን በማንቆለጳጰስ የሚታወቀው የቴሌቪዥን ጣቢያ ለረጅም ጊዜ ከሚዲያ ጠፍቶ የቆየውን ጀዋር መሐመድን በምናደንቀውና በምንወደው ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ አማካኝነት አፈላልጎ ደሬ እስከ ኬኒያ ናይሮቢ ተጉዞ ለሕዝብ ማቅረብ ችሏል ማለፊያ ነው
ጀዋር በቃለ መጠይቁ ከነበረበት እብደት ወጥቶ የሰከነ መሆኑን ሊያሳየን ቢሞክርም በቃለ መጠይቁ ላይ ያነሳቸው አንዳንደ ነጥቦች አነጋጋሪ ናቸው፤የፖለቲካ ምሁር ነኝ ብሎ በመመፃደቅ የሚታወቀው ጀዋር መሐመድ ሆን ብሎ ወይም ስቶ ያነሳቸውን ነጥቦች በዝምታ ማለፍ ተገቢ አይሆንም አንድ ጉዳይ ብቻ ላንሳ
ጀዋር መሐመድ በቃለ መጠይቁ ክፍል አንድ ማጠናቀቂያ ላይ አንድ ወሳኝ ጉዳይ እንደ ቀላል ነገር ጣል አድርጓል መልዕክቱ ምን ለማለት እንደተፈለገ ይታወቃል
“የፖለቲካ ስራው በመከላከያ ላይ ወድቋል” ነበር ያለው ጀዋር ቃለ መጠይቁን በማጠናቀቅ ደረጀ ኃይሌን ቡና ለመጋበዝ ሲያኮበኩብ፤ጀዋር “በአሁኑ ወቅት የፖለቲካ ስራው በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ወድቋል”ያለው በምክንያት ነው
በተገኘው አጋጣሚ እንዲህ ዓይነት መልዕክት ማስተላለፍ ጽንፈኛ ኃይሎች ስሙን በማጉደፍ የዘመቱበት ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ለብልፅግና ፓርቲ የወገነና ፓርቲው መስራት ያለበትን የፖለቲካ ስራ በማከናወን ላይ ይገኛል ብሎ መክሰስ ነው፤መልዕክቱ በቀጥታ ይህን ላለማለት በስልት የተላለፈ መልዕክት መሆኑን መገንዘብ ይገባል!ተው እንጂ ጀዋር!የነገርን ብልት የማውቀው እኔ ብቻ ነኝ አትበል!
አረ ለመሆኑ ጀዋርዬ የሚደረግብኝ ምንም ጫና የለብኝም ብለሃልና ምነው በደህና! ፊንፊኔን ትተህ ኬኒያ ናይሮቢ ውስጥ ለመመሸግ ተገደድክሳ? ደሬ በነካ እጅህ በአንዳንድ ነገር ፕሮግራምህ ላይ ግልጥ ያልሆኑ አንዳንድ ነገሮችን ታቀርብ ይሆናል በሚል ተስፋ መጠበቅ መልካም ነው

Post a Comment

0 Comments