ጥምቀት በዓላችን የሁላችን!

 



ፊንፊኔ ጥር 10/2016(YMN) ጥምቀት የሁላችን በዓል ነው! እንዲህ የሚባለው በምክንያት ነው፤ምክንያቶቹ የተለያዩ ናቸው እስኪ አንድ በአንድ ዘርዘር አድርገን እንያቸው፤ጥምቀት እንደ ሌሎቹ በዓላት ሁሉ በሁሉም ኢትዮጵያዊያን በአብሮነት የሚከበር አመታዊ መዓል ነው

በእምነቱ ረገድ ጥምቀት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች በዓል ቢሆንም ኢትዮጵያዊያን የሌላ እምነት ተከታዮችም በዓሉን እንደ ራሳቸው በዓል ይመለከቱታል፤በዚህ ምክንያት የጥምቀት በዓል ሞቅ ደመቅ ብሎ እንዲከበር ይሻሉ ለዚህም የበኩላቸውን ድጋፍ ያደርጋሉ በሁሉም ረገድ ይተባበራሉ

ይህ ባይሆን ኖሮ የሌላ እምነትና ሃይማኖት ተከታዮች የጥምቀት በዓል በሰላማዊና የሃይማኖቱን ስርዓት ጠብቆ እንዲከበር አይደግፉም፤የበዓሉ ስርዓት የሚፈፀምባቸውን ቦታዎች አያፀዱም፤በማንኛውም ሁኔታ አይተባበሩም ነበር!ምን ቦጣቸውና!

ነገር ግን በዓሉ ልክ እንደሌሎቹ በዓላት እንደ ሞሊድ፤እንደ አረፋ፤እንዳ ረመዳንና ሌሎች በዓላት ሁሉ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን የአብሮነት ማሳያ በዓል ስለሆነ ጥምቀትም በሰላማዊ ሁኔታ ተከብሮ እንዲያልፍ ጽኑ ፍላጎት አላቸው፤በዚህ ተጨባጭ ምክንያት ዓመታዊው የጥምቀት በዓል የሁሉም ኢትዮጵያዊያን በዓል ነው ማለት ይቻላል!ምክንያቱም አንዱ ያለ ሌላው ድጋፍና መተባበር ሊኖር አይችልምና

ሌላው ጥምቀት የሁላችን በዓል ነው!የሚያስብለው ተጨባጭ ምክንያት ጥምቀት ከአምስት ዓመታት በፊት የዓለም ቅርስ ሆኖ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና አግኝቶ የተመዘገበ በመሆኑ ኑው፤በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና አግኝተው የተመዘገቡ የገዳ ስርዓትን ጨምሮ ሌሎችም የማይዳሰሱ ቅርሶቻችን የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሃብት ናቸው፤ሁላችንም የምንኮራባቸው ሃብቶቻችን ናቸው

ቅርሶቹን ለመጎብኘት ከሚመጡ ቱሪስቶች የሚገኘው ገቢ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሕይወት እንዲሻሻልበት የሚገኝ የሀገር ገቢ ነው፤አስተማማኝ የሀገር ገቢ ሲገኝ ደግሞ በተዘዋዋሪ መንገድ ዜጎችን ማበልፀጉ የማይቀር ነው! ይህን እውነት በደንብ መያዝ ይገባል!የተመዘገቡ ቅርሶቻችን ቀጣይነት ያለው ገቢ ሊያስገኙልን የሚችሉት ደግሞ ተንከባክበን ይዘን መጠበቅ ስንችል ብቻ ነው

በሌላ በኩል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያን ሃይማኖታዊና ሌሎች የአደባባይ ላይ በዓልትን ተገን በማድረግ ግጭት ፈጥሮ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚደረገው መቅበዝበዝ አስተዛዛቢ ሆኖ ቀጥሏል አሳዛኝ ነው!መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህን ሁኔታ ተመልከቶ ቀደም ሲል ታዝቧል፤አሁንም በታዘብ ላይ ይገኛል

በፖለቲካው ገበያ ላይ ሃሳቡን ለሕዝብ በማቅረብ ተቀባይነት ያጣ ቡድን ሁሉ በአደባባይ በዓላት ላይ ጥቃት በማድረስ ተሰሚነት ለማግኘት ይሯሯጣል፤የከሰረው ቡድን ኃይልን በመጠቀም መንግስት በጉልበት ከስልጣን እንዲወርድለት ይቅበዘበዛል፤ግን ደግሞ አይሳካለትም፤ቀደም ሲል አልተሳካለትም ወደፊትም እንደማይሳካለት ይታወቃል

የአደባባይ ላይ በዓላትን ተገን በማድረግ ተሰሚነትን ለማግኘት መሯሯጥ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለው ይታወቃል፤መላው ሕዝብ በሰላም ወጥቶ በሰላም መግባትን ይሻል፤ለዚህም ሲል ከመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ጎን በመሰለፍ ሙሉ ድጋፉን በመስጠት ላይ ይገኛል፤አሁን የተለመደው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል የሚያስፈልግበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን

የኢትዮጵያ ጠላቶች የከሰሩ የውስጥ ተላላኪዎችን በመጠቀም የትኛውንም አጋጣሚ ከመጠቀም ወደ ኋላ እንደማይሉ ይታወቃል ስለዚህ የዘንድሮው የጥምቀት በዓል በሰላማዊ ሁኔታ ተከብሮ እንዲያልፍ ሁሉም ኃላፊነቱን መወጣት ይጠበቅበታል!መልካም የከተራ፤የጥምቀትና የአስተሪዮ ማሪያም በዓል ይሁንልን!

 

 

Post a Comment

0 Comments