ፊንፊኔ ታህሳስ 23/2016(YMN) በእውነት የድንጋጤ ስሜቴን እንዴት እንደምገልፀው አላውቅም።በታሪክ "የኃይማኖት መሪዎች" በኢትዮጵያ ላይ ግፍ እንደፈፀሙ የማውቀው የኢጣሊያ ወራሪ ሠራዊት ኢትዮጵያን ለመውረር ሲዘምት የሮማው ካቶሊካዊ ቤተክርስቲያን ጳጳስ ቡራኬ ሰጥተውና ወረራውን ባርከው መሸኘታቸውን ነው።ከዚህ ውጪ በተለይ "የኢትዮጵያ ኃይማኖት አባት"የሀገሩ መሪ "በጥይት ግንባሩን ተብሎ እንዲገደል"ሲሰብክ ቡራኬ ሲሰጥ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም።በተለይ ወደስልጣን በመጣ ማግስት በሁለት ሲኖዶስ ተከፍሎ ሲባላና አንዱ ሌላውን ሲያወግዝና ሲገዝት የኖረን "የኃይማኖት አባት"ተንበርክኮ በመለመንና በማስታረቅ ታሪክ የሠራን መሪ"ግንባሩን ብላችሁ ግደሉት"ማለት ከሰይጣን እንጂ ከሰብአዊ ፍጡር የሚጠበቅ አይደለም።እርስ በእርሱ ሲባላ የኖረን ሲኖዶስ አንድ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ስደተኛውን ሊቀ ጳጳስ ከነአጃቢዎቹ በራሱ አውሮፕላን አብሮ ወደ አገር ቤት በማስገባት በክብር ያስቀመጠን መሪ "ግንባሩን በጥይት ብለህ ግደል"ብሎ መስበክ ይሁዳነት ከመሆን አልፎ ህሊና ሊያስበው ከሚችለው በላይ ነው።በታሪክ የኢትዮጵያ ኃይማኖት አባቶች የሚታወቁት አገር በባዕድ ኃይል ሲወረር ወራሪን በማውገዝ በአደባባይ በጥይት ሲደበደቡ ነው።ህዝብ ለፈጣሪውና ለመሪው እንዲታዘዝ ሲሰብኩ ነው።ሰላም እንዲሰፍን÷የተጣላ እንዲታረቅ÷የበደለ እንዲክስ÷የተበደለ ይቅር እንዲል መዕምኑን ሲያስተምር ነው።ከዚህ ውጭ የሀገር መሪ በአመፀኛ "ግንባሩን ተመቶ እንዲገደል"ምድራዊ ብያኔ የሰጠ ዳቢሎስ ታይቶ አይታወቅም ነበር።ይህ ዳቢሎስነቱን በኃይማኖታዊ ካባና ቆብ ሸፍኖ ዕድሜውን የጨረሰና መቃብሩ የተቆፈረ ሽማግሌ እንደዘመነኞቹ ደም ነጋዴዎች ፖለቲካዊ አቋም ከመያዝም አልፎ የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትር "ግንባሩን ብላችሁ ግደሉና ጀግና ሁኑ÷መንግስተሰማያትንም ውረሱ"እስከማለት ደረሰ።እጅግ አስደንጋጭ÷አሳፋሪና ታሪክም ሲሸማቀቅበት የሚኖር እርኩስነት መሆኑ አያጠራጥርም።የብዙ ዳቢሎሶች መጠለያና የእልቂት መስበኪያ የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ኃይማኖታዊ ካባዋን ደርቦና ቆቧን ደፍቶ÷ፅላተ ታቦትም ከጎኑ አሸክሞ "ግንባሩን ብላችሁ ግደሉ"ያለውን ዳቢሎስ እየታዘበች ዝምታን ከመረጠች ከባድ ኃይማኖታዊ ኪሳራ ውስጥ መግባቷና በለውጥ ፈላጊው ትውልድ ዘንድ ለትዝብት መዳረጓ አይቀርም።
ከዚህም በላይ አሁን አገሪቱ የምትመራበት ህገመንግስት "ኃይማኖትና መንግስት የተለያዩ"መሆናቸውን ይደነግጋል።ኃይማኖት በመንግስት÷መንግስትም በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገባ ይከለክላል።ይህ ካባ ለባሽ ዳቢሎስ የፈፀመው ወንጀል ሰማያዊም ምድራዊም ነው።ካባ ለባሹ ዳቢሎስ እጅግ በመረረ ጥላቻና ጭካኔ"ጠቅላይ ሚኒስትሩን ግንባሩን ብላችሁ ግደሉ"ሲል እየዘገነነን አዳመጥን ህዝብ እንዲያምፅና እርስ በእርሱ እንዲፋጅ÷አገር ጠባቂው ሰራዊት መሪዎቹን ገድሎ አገሪቱን ለጠላቶቿ መጫወቻነት እንዲያስረክብ በድፍረት ሰበከ።ይህ ካባ ለባሽ ዳቢሎስ ይህንን ዘግናኝ ምድረዊና ሰማያዊ ወንጀል ሲፈፅም አህዛቡ አጨበጨቡለት።ትንንሾቹ ተከታይ ዳቢሎሶቹ በማህበራዊ ሚዲያ አስተጋቡለት።"ግንባሩን ብለህ ግደል"ያለን ጭራቅ"ቆራጥ የኃይማኖት አባት"አሉና ውዳሴ አዘነቡለት።"ክፉን በክፉ አትቃወሙ÷ጠላታችሁን እንደራሳችሁ ውደዱ"እየተባለ ሲሰበክባት በኖረች ኃይማኖታዊ አገር ላይ"መሪህን ግንባሩን ብለህ ግደል"ሲል ዳቢሎስ ሰበከ።ከዚህ በላይ እነአልቃይዳ÷አይሲስ÷አልሸባብ ..ምን ሰብከው "አሸባሪ" እንደተባሉ አላውቅም።እነሱም "ግደሉና ጀነትን ውረሱ"ነው የሚሉት።የኦርቶዶክሱ ዳቢሎስም "ግንባሩን በልና ጀግና ሁን "ነው ያለው።እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ!ይህ ዘመን÷ይህ ለውጥ ስንቱን አረመኔ÷ስንቱንስ ኃይማኖተኛ መሳይ ጭራቅ አደባባይ አውጥቶ አሰጣ ፈጣሪ ምህረቱን ይዘዝልን።
በዓለምነው አበበ
0 Comments